Abstract:
የብራና መጻሕት በቁጥር፣ በዓይነትና በይዘት ከገዳም ገዳም የተለያዩ ናቸው፡፡ እኒህን
መጻሕፍት ጠብቆ ለማቆየትና ለአጠቃቀምና ለጥናት ምቹ ለማድረግ መጻሕፍቱን ዘርዘሮና
አደራጅቶ ማስቀመጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ስለዘህ ጥንታዊ የብራና
መጻሕፍት የመዘርዘርና የማደራጀት ዓላማው፣ መረጃ እና እውቀትን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን
መጻሕፍቱን በመጠበቅ ከከፌተኛ ብልሽት፣ ስርቆትና ዘረፋም ይከላከላል ማለት ነው፡፡ ስለኾነም
አጥኚው በጎረፍ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የሚገኙ 12 የነገረ ቅደሳን የብራና መጻሕፍትን
ለማጥናት ሞክሯል፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ ያነሳሳው ዋናው ምክነያትም በውስጡ 67 የሚደርሱ
የብራና መጻሕፍት ቢኖሩትም በሌሎች አጥኚዎች ባለመታየቱና ባለመጠናቱ ነው፡፡ አጥኚው
በዓይነታዊ የጥናት ሥነ ዘዴ፣ የብራና መጻሕፍቱን እንደ መጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ
በመጠቀም ፣ሌሎች ምሁራን በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ላይ ያጠኗቸውን ጥናቶች ደግሞ
እንደ ኹለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ተጠቅሞ ጥናቱን አካሂዷል፡፡ በጥናቱ መሠረትም የብራና
መጻሕፍቱ አብዛኛዎቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ ሲገኙ የተወሰኑት ደግሞ በተለያዩ ሁኔታና ደረጃ ላይ
ተቀዳደውና ተገነጣጥለው ይገኛሉ፡፡ ስለኾነም ጥናቱ የብራና መጻሕፍቱ አቀማመጥ፣አጠቃቀምና
ጥበቃ ምን መኾን እንዳለበት ለሚመለከታቸው አካላት፣ ማለትም ለገዳሙ መነኮሳት፣ለቤተ
ክህነትና ለባህልና ቱሪዝም የይኹንታ አስተያየቱን አቅርቧል፡