Abstract:
ይኽ ጥናት በአቡነ መዝገበ ሥላሴ የብራና ገድል ላይ ይዘት በመተንተን የተሠራ ነው፡፡ ዐቢይ
ዓላማውም ይዘቱን በመተንተን ኹለንተናዊ ፋይዳውን በማሳየት ተካናውኗል፡፡ ይህንንም ዓላማ
ለማሳካት በዋናነት የብራናውን ገድል ቀዳማይ የመረጃ ምንጭ በማድረግ ሌሎች ኹለተኛ የመረጃ
ምንጮችን በመጠቀም በዓይነታዊ የጥናት ዘዴ ትንተናው ተከናውኗል፡፡ ጥናቱ በአምስት ምዕራፎች
የተሠራ ሲኾን የመጀመሪያው ምዕራፍ የጥናቱን ጠቅላላ መግቢያ በመያዝ ዳራውንና መነሻ
ሐሳቡን፣ ዓላማውንና ጥቅሙን እንዲኹም ወሰኑንና ዘዴውን ይገልጻል፡፡ በምዕራፍ ኹለት ጥናቱ
ከፅንሰ ሐሳብ አኳያ የገድላት ይዘትንና ጥቅማቸው እንዲኹም ከጥናቱ ጋር አንድነትና ልዩነት
አላቸው የተባሉ ተዛማጅ ጽሑፎችን ጨምሮ በማካተት ይዟል፡፡ በምዕራፍ ሦስት ደግሞ የገድሉ
አጠቃላይ ይዘት ምን እንደሚመስል ይናገራል፡፡ ምዕራፍ አራትን የጥናቱ ዋና ማዕከል በማድረግ
ስለ አቡነ መዝገበ ሥላሴ የሕይወት ታሪክ ልደትና ስያሜ፣ ዕድገትና የትምህርት ኹኔታ፣ ክህነት፣
ምንኵስና አገልግሎት፣ አስተዋፅዖና ቃል ኪዳን እንዲኹም ዕረፍተ ሕይወት ቀርቦውበታል፡፡
በተጨማሪረም በገድሉ ውስጥ የተጠቀሱ የሥነ ጽሑፍ ጉዳዮች ከእነማስረጃቸው ተተንትነውበታል፡፡
በአጠቃላይ ጥናቱ ገድድሉ ከሃይማኖታዊ ፋይዳቸው በተጨማሪ ሊኖራቸው ስለሚችል ማኅበራዊ፣
ፖለቲካዊ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ሌሎችም ጥቅሞች እንዳሉትም የቀረበበት እና ለተጨማሪ ተግባራት
ምክረ ሐሳብ የተጠቆመበት የጥናቱ መደምደሚያ ደግሞ ምዕራፍ አምስት ነው፡፡