Abstract:
ይህ ጥናታዊ ጽሐፍ የሚያተኩረው በገድለ ዮሓንስ ዘውራ ኢየሱስ የይዘት ትንተና ሊይ ነው፡፡ ሇዘህ ጥናትም አገልግሎት ሊይ የዋለዉ የጻዴቁ ዮሓንስ ዘውራ ኢየሱስ የብራና ገድል ሲኾን ገድሉም የተገኘዉ በሜጫ ወረዲ በሚገኘው ውራ ኢየሱስ አንድነት ገዳም መኾኑ በጥናቱ ተቀምጧል፡፡ የጥናቱ መግቢያ፤ አነሣሽ ምክንያቶች፤ ያለዉ ሲኾን ዋና ዋና ምክንያቶቹ ካሁን በፊት ያልተጠና መኾኑና አጥኚው ገድለ በሚገኚበት ገዳም አካባቢ ተወሊጅ በመኾኑ የጻዴቁ ዮሓንስ ታሪካዊ አመጣጡ ያወዛግበዉ ስለነበረ ነው፡፡ የጥናቱ ዋና አላማና ዝርዝር አላማዎች፤ በጥናቱ የተመለሱ መሠረታውያን ጥያቄዎች፤ የጥናቱ ጠቀሜታዎች፤ ለአጥኚዉ ያጋጠሙት ችግሮች እስከ መፍትሄያቸው በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ስለገዴሊት ታሪካዊ አመጣጥ፤ ስለተጻፈበት ቃንቃ፤ ስለገዴሊት ክፍሎች፤ ከነአላማቸውና ከነጠቀሜታቸው እንዲሁም በማን እና መቼ እንደተጻፈ በክለሳ ድርሳናት የተብራራ ሲኾን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴውም ሰነድ በመፈተሸ፤ ፎቶ ካሜራ በማንሣትና እስከቦታው ድረስ የዘህ ጥናታዊ ጽሐፍ አጥኚ በመኼድ አካሊዊ ምልከታ መኾኑንም ተገልጧል፡፡ ጥናቱም አይነታዊ የምርመር ዘዴን የተከተለ ሲኾን የመረጃ ምንጮቹም የጻዴቁ ዮሓንስ የብራና ገድለን አንደኛ የመረጃ ምንጭ፣ የኅትመቱ ገድለ እና ሌሎች ከገዴለ ጋር ተዙማጅነት ያሊቸው ሰነድች እንሆ ኹለተኛ መደብ የመረጃ ምንጭ በመኾን አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ የገዴለ ውስጣዊ ይዘቱም በያይነቱ ተመድቦ ይዘቱ ሲተነተን ጻዴቁ ቅደስ ዮሓንስ የሃይማኖት ሰው፣ ማኅበራዊ ግንኙነት ያሊቸው ሰው ከመኾናቸዉ በተጨማሪ የፖለቲካ ሰው እንደነበሩም በትንተናው ተካቷል፡፡ ጻዴቁ ዮሓንስ ሦስቱ ገዳማትን በመመሥረት ለሀገር አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲኾኑ የአንበሶች እና ዴንጋይቱ አስደናቂ ሥራም የእንስሳትና የግኡዙን እንዱሁም ይቅደሳን ሰዎች አስተዋጽ በሚሌ ርእሰ ጉዲይ ተብራርቷሌ፡፡ የውራ ኢየሱስ ገዲም የስም ስያሜ ውሮ ይባል በነበር ባላባት ስም ውራ እንደተባለ በገዴለ ገጸ ንባብ ውስጥ ተገኚቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ጀምራ ድንጋይቱ እያበራች አምጥታ ከጉታ ዲጋሉ ተብል ከሚጠራው ቀበላ በተለይ አብሪ የሚባለው ጎጥ ተራራማና ድንጋያማ ቦታ ሲኾን እስካሁን ድረስ አብሪ ተብሎ ሚጠራበት ምክንያት እያበራች በመጣችዋ ድንጋይ መኾኑም በግድለ የይዘት ትንተና ተመልክቷል፡፡ከፈጣሪዉ የተቀበለችዉ ቃል ኪዲኖች ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ የገድለ ጸሁፉ ስምም የማነ ክርስቶስ እንሚባል በጥናቱ ተካቷል፡፡ የገድለ ጸሁፊ ያጻጻፊ ስልቱ በዘይቤ አይነቶች ተከፋፍለው በትንተናው ተብራርተዋል፡፡በመጨረሻም የዘህ ጥናታዊ ጽሐፍ ጠቅላላ ይዘት እና ትንታኔ አጠርና ጠቅለል ተደርጎ በኹለት ገጽ ተከልሶ ተጠቃሎል፡፡ በተጨማሪም አጥኚው ለጥናታዊ ጽሐፉ ማጠቃለያ ከሰጠ በኋላ በይሉኝታ ሀሳቦች በተለይ ገዴሊትን ሚያሳትሙ አባቶች የታሪክ ተፋልሶ እንዲይፈጠር የብራና ገዴለን በደንብ ቢያዩት በማለት ጥናታዊ ጽሐፈን አጠቃሎል፡፡