Abstract:
ይኽ ጥናት “ንጽጽራዊ የዘር አወጣጥ ጥናት በዋዴሊ፣ በዋሸራ እና በጎንጅ የቅኔ አብያተ ጉባኤያት” በሚሌ ርእስ ሊይ ተመሥርቶ የተሠራ ሲኾን፣ ዋና አላማዉም በሦስቱ አብያተ ጉባኤያት መካከል የዘር አወጣጥ ልዩነት መኖር እና አለመኖሩን መመርመር ነው፡፡ አጥኚዉን ለዚህ ጥናት እና ምርምር ሥራ ያነሣሣዉ አቢይ ምክንያት በሦስቱ የቅኔ አብያተ ጉባኤያት ውስጥ ተምረው በወጡ ምሁራን የተጻፈ የግእዛ መዝገበ ቃላት፣ የሰዋስው መጻህፍት እና ከሦስቱ አብያተ ጉባኤያት ውጭ በኾኑ ምሁራን የተጻፈ መጻህፍት የዘር አወጣጥ ልዩነት በማሳየታቸው ነው፡፡ ይኽ ጥናትም ከግብ ይደርስ ዘንድ አይነታዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ጠቃሚ መረጃዎች በሰነድ ፍተሻ እና በቃለ መጠይቅ ከተሰበሰቡ በኋላ አላማ ተኮር ንሞናን በመጠቀም መረጃዎቹ በገላጪ ንጽጽራዊ የመረጃ መተንተኛ ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ ለጥናት በተመረጡ መጻህፍት ውስጥ ዘሮች ከሥርወ ቃላት ላይ ሲመሠረቱ የአሥራወ ቃላቱ መነሻ፣ ሁለት ተከታታይ መነሻ፣ መድረሻ፣ እንዲኹም መነሻ እና መድረሻ ፊደላት ከዘሮች ላይ ተጎርደው ታይተዋል፡፡ እንዲኹም በዘር መካከል ባእድ ፊደል በመጨመር የተመሠረተ ዘር፣ የደጊመ ፊደል ቅርጽ ከለለው ሥርወ ቃል ባለ ደጊመ ፊደል ዘር የተመሠረተ ዘር እና ድርብ ምእላዳትን ይዞ የተመሠረተ ዘር መኾኑን ማረጋገጥ ተችላል፡፡ በጥናቱም በትርጉም እና በፊደል የማይገናኝ የዘር አወጣጥ፣ ከፊል ፊደላዊ እና ምስጢራዊ የዘር አወጣጥ፣ ሙሉ ምስጢራዊ የዘር አወጣጥ፣ በዘር መካከል ባእድ ፊደል በመጨመር የተመሠረተ ዘር፣ ከነጠላ ሥርወ ቃል በደጊመ ፊደል የተመሠረተ ዘር እንዲኹም ድርብ ምእላዳትን በመያዛ የወጣ ዘር የሚለት ርእሰ ጉዲዮች በተገቢው መንገድ ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ በጥናታዊ ግኝቱም በሦስቱ የቅኔ አብያተ ጉባኤያት መካከል እና እንዲኹም በሌሎች ምሁራን ዘንድ የዘር አወጣጥ ልዩነት እንዳለ ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም በሥርወ ቃል የሚጀምር፣ የተውሶ ቃላትን፣ ነባር ቃላትን እና ዘርን ለይቶ የሚያቀርብ የግእዛ መዝገበ ቃላት የዘመናዊ እና የአብነት የትምህርት ተቓማትን ማእከል አድርጎ ቢዘጋጅ እና ተደራሽ የሚኾንበት መንገድ ቢመቻች፤ ማንኛዉም የዘር አይነት ከሥርወ ቃል ሲወጣ በፅንሰ ሀሳብ ሳይኾን፣ ትርጉምን እና መልእክት ፊደልን ብቻ መሠረት ያደረገ ቢሆን፣ ግላዊ የኾነ የዘር አወጣጥን ለመቀነስ ሲባል፣ የግእዝመዛግብተ ቃላት ሲዘጋጁ የአርትዕት ሥራ የሚሠራ ተቃም ቢቃቃም፣ በግእዝ ቃንቃ ዙሪያ የተሠሩ ጥናቶች እና ግኝቶቻቸው ለሚመለከታቸው ግለሰቦች እና ተቃማት እንዲደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቃማት ኀላፊነታቸውን ቢወጡ መልካም መኾኑን የሚጠቁሞ ሀሳቦች ተካተው ቀርበዋል፡፡