BDU IR

በቻግኒ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ያሉ የብራና የእጅ ጽሑፎች መዘርዝር

Show simple item record

dc.contributor.author ገብረጻድቅ, ፍሬስብሐት
dc.date.accessioned 2025-05-08T11:30:50Z
dc.date.available 2025-05-08T11:30:50Z
dc.date.issued 2017-01
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/16724
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በቻግኒ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኙ የብራና የእጅ ጽሑፎችን መዘርዝር መሥራት ነው፡፡ በመሆኑም አጥኚው በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ካሉት አጠቃላይ 71 ልዩ ልዩ መጻሕፍት መካከል ጥናቱ የሚያተኩርባቸውን ዘጠኝ የብራና መጻሕፍትን ብቻ በመምረጥ የውጭ አካላዊ መረጃቸውን በተገቢ ኹኔታ በመግለጽ፣ በውስጥ የያዙትን ዋናዋና ክፍል በመዘርዘር፣ የብራና መጻሕፍቱን ቅጠሎች፣ የጥራዝ ብዛቶች፣ ዐምዶች እንዲሁም በየምዕራፉ መጀመሪያና መጨረሻ ያሉትን ይዘቶች በማየት አይነታዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም የጥናቱን ውጤት ጽፏል፡፡ የጥናቱ አነሣሽ ምክንያት፣ዓላማው፣ የጥናቱ ዘዴ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ስልት እንዲሁም ተዛማጅ ጽሑፎች ተጠቅሰዋል፡፡ በአጥኚው የተጠኑት ሁሉም መጻሕፍት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ በጥናቱ መሠረትም አብዛኞቹ የብራና መጻሕፍት ከአቶ ነጋሽ ወዳጄ የተበረከቱ ናቸው፡፡ የአቀማመጥ ኹኔታቸውም ጥሩ ስላልነበረ መጽሐፈ ብርሃን በርጥበት ምክንያት ብራናዎቹ ጠቁረዋል እንዲሁም ተቆራርጠዋል፡፡ መዝሙረ ዳዊቱም ጠርዝ ጠርዙ ተጎድቷል፡፡ ሌሎች ግን በጥሩ ሁኔታ ናቸው፡፡ ወንጌሉና ተአምረ ማርያም በዐበይት በዓላት ይነበባሉ ሌሎች ግን የመነበብ እድል ተነፍገዋል፡፡ አጥኚዉ በመጨረሻዉ በማጠቃለያ ያጠቃለለ ሲኾን ከጥናቱ በመነሣት የብራና መጻሕፍቱ ለአንባብያን ተደራሽ ቢሆኑ ሚል የይኹንታ ሐሳብ አስቀምጧል፡፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject Geʽez en_US
dc.title በቻግኒ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ያሉ የብራና የእጅ ጽሑፎች መዘርዝር en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record