Abstract:
ይህ ጥናት በአቡነ ተክለ አልፋ የብራና ገድል ላይ የይዘት ትንተና የተሠራ ነው፡፡ ይህንንም ጥናት ለማሳካት በዋናነት ጎፍጭማ ቅደስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ አልፋ ደብር የሚገኘውን የብራና ገድል የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሲኾን የታተሙም ኾነ ያሌታተሙ ጽሐፎችን እንዱሁም ቃሇ መጠይቆችን በኹሇተኛ ዯረጃ የመረጃ ምንጭነት በመጠቀም ጥናቱ ተከናውኗል፡፡ ጥናቱ በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈል ሲኾን፣ በምዕራፍ አንድ የጥናቱ ዳራ እና መነሻ ሐሳቡን፣ የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት፣ የጥናቱ ዐላማና ጠቀሜ፣ የጥናቱ ጥያቄዎች፣ የጥናቱ ወሰን እንዱኹም ውስንነት ይዟል፡፡ ምዕራፍ ኹለት ጥናቱ ከፅንሰ ሐሳብ አኳያ የገድላትን ይዘት፣ ክፍሎች፣ ጥቅማቸውን የተጻፋበትን ቋንቋ፣ ታሪካዊ አመጣጥ እንዲኹም ስለ አቡነ ተክለ አልፋ ተዛማጅ የኾኑ ጽሑፎችን ይዟል፡፡ ምዕራፍ ሦስት የጥናቱን ዘዴ፣ የገድሉን ውጫዊ እና ውስጣዊ ይዘት የሚያሳይ ሲኾን የዚህ ጥናት የምርምር ዘዴ ዐይነታዊ የምርምር ዘዴ ነው፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሰነድ ፍተሻና ቃለ መጠይቅ ሲኾን የመረጃ አተናተን ዘዴው ገላጭ የአተናተ ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ ምዕራፍ አራት የጥናቱ ዋና ማዕከል ሲኾን ስለ አቡነ ተክለ አልፋ የሕይወት ታሪክ የሥጋ ልደት እና የቆብ ልደት እስከ ዕረፍተ ሥጋ ያለው ታሪክ ተብራርቶበታል፡፡ አቡነ ተክለ አልፋ በአኹኑ የቦታ አከላለል በምሥራቅ ጎጀም ዞን ደብረ ኤሌያስ ወረዳ ጎፍጭማ ቀበሌ ተወልደው በአካባቢያቸው በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ምናኔያቸውን ጀምረው ሲጋደሉ ከቆዩ በኋላ ወደ ዲማ ቅደስ ጊዮርጊስ ገዳም በመኼድ በገዳሙ የተለያዩ ተጋድሉዎችን ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ በዚኹ ገዳም በ75 ዓመታቸው ታኅሣሥ 8 ቀን ዐርፈዋል፡፡ የአቡነ ተክለ አልፋ የቆብ አባታቸው የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ፊሌጶስ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ አልፋ በሕይወተ ሥጋ እያለም ይኹን በሕይወተ ሥጋ ካለፋ በኋላ ብዙ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገድላቸው ያሳያል፣ ካደረጉት አስተዋጽኦ ውስጥ ክርስትናን ማስፋፋት፣ የመነኯሳቱን አኗኗር መቀየር፣ ቅርስ ጥበቃ፣ ተአምር፣ ፈውስ እና ቃል ኪዲን ናቸው፡፡ የገድሉ ሥነ ጽሑፋዊ ፋይዳ ሲታይ ሃይማኖታዊ ፋይዳዉ ዶግማ እና ቀኖና፣ ማኅበራዊ ፋይዳዉ በሽተኛን መጠየቅ እና ማስታመም፣ ለሌለው መስጠት ወይም ማካፈል፣ አራስ ጥየቃ እና ወላጅ አልባ ልጆችን ማሳደግ፣ ባህላዊ ፋይዳዉ ሠርግ፣ እንግዳን መቀበል፣ ለቅሶ ወይም ኀዘን፣ ጠንካራ የሥራ ባህል፣ ግጭትን መፍታት፣ መከባበር እንዲሁም ስንብት፣ አስተዳደራዊ ፋይዳዉ ፍትሐዊነት፣ ካሳ አከፋፈል፣ ሀቀኝነትና አለማዳላት ሲኾኑ ታሪካዊ ፋይዳዎችም ተዳሰውበታል፡፡ የገለለ የቋንቋ አጠቃቀም ሥናይ የቋንቋ ክፍል አንዱ የኾነው ዘይቤ የተዳሰሰ ሲኾን ይህም ገድሉ ሰውኛ ዘይቤ፣ አነጻጻሪ ዘይቤ እና ምስያ
ዘይቤዎችን እንደተጠቀመ ያሳያሌ፡፡ በመጨረሻም በምዕራፍ አምስት የጥናቱ ማጠቃለያ እና የአጥኝዋ ምክረ ሐሳብ ሰፍሮበታል፡፡