Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በውዲሴ ማርያም ውስጥ የሚገኙ ለጽሑፋዊ አርትዖት መነሻ
የሚሆኑ ሐሳቦችን መርምሮ ማሳየት ነው። የዚህ ጥናት አነሣሽ ምክንያትም በሥነ
ጽሑፍ እና በሥነ ልሳን ትምህርቶች ውስጥ ከሀገራዊ መነሻና ምንጭ ይልቅ የውጭ
ምንጮችን መጠቀም እጅጉን የተለመደ በመሆኑ፣ እንደ መነሻ የሚያገለግለ የአንድምታ
ትርጓሜ ስልቶችን አደራጅቶ ለዘመኑ የሥነ ልሳን ትምህርት እንዲጠቅሙ ማድረግ
ባለመቻለ ነው። ይህንንም ዓላማ ከግብ ለማድረስ የመንበረ መንግሥት፣ የግምጃ ቤት፣
የመካነ ኢየሱስ፣ የዲማ፣ የበዓታ፣ የምስካየ ኅዙናን፣ የትንሣኤ ዘጉባኤ እትምና ሌሎች
ባለቤታቸው ያልታወቁ አብነቶች ተሰብስበው ሰነድ ፍተሻ ተካሂዶባቸዋል።
በተጨማሪም የአርትዖት ዓላማንና ተግባርን ለማወቅ፣ ቀድሞውኑ በድርሰቶቹ ላይ
የተከሰቱት የቋንቋና የምስጢር ግድፈቶች ለምን እንደተከሰቱ ለመረዲት ለተመረጡ
የአንድምታ እና የቅኔ መምህራን ቃለ መጠይቅ በማቅረብ በሰነድ ፍተሻው ግልጽ
ያልሆኑት ሐሳቦች ግልጽ እንዲሆኑ ተደርጓል። የተሰበሰቡት መረጃዎችም ንጽጽራዊ
የመረጃ ትንተና ዘዴን በመጠቀም በገላጭ የመረጃ አታናተን ስልት ተተንትነዋል።
የጥናቱ ውጤትም ለዘመኑ የአርትዖት ስልት መነሻ የሚሆኑ የአርትዖት ተግባራት
በውዲሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ ውስጥ እንደሚገኙ፤ ምንም የመተርጕማኑ ዓላማ
መጽሐፉን በግልጽ መተርጏም ቢሆንም እግረ መንገዲቸውን በገጸ ንባቡ ሊይ የሠሩት
አርትዖት ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖረው ቢደረግ ጠቃሚ እንደሆነ በሰነድ ፍተሻውም
በቃለ መጠይቁም ውጤት ተገልጧል። አጥኚው ባደረጋቸው የሰነድ ፍተሻዎች በውዳሴ
ማርያም አንድምታ አብነቶቹ መካከል መጠነኛ ልዩነት እንዳለ ጥናቱ አመልክቷል።
የዚህን ጥናት ጥቆማ መሠረት በማድረግ በየጉባኤ ቤቱ እና በየገዳማቱ የሚገኙ ልዩ
ልዩ የአንድምታ አብነቶች በሙያው ልሂቃን ጥናትና ምርምር ቢደረግባቸውና
ለዘመናዊ ትምህርቶቻችን የሚያገለግሉበት ስልት እንዲዘጋጅ ቢሆን ሀገር በቀል የሆነ
የሥነ ጽሑፍና የቋንቋ ትምህርት ይኖረናል የሚል ጥቆማ ቀርቧል። በመጨረሻም
በአብነቶቹ መካከል የሚታዩ ልዩነቶች ማጥበብ የሚያስችሉና በአንድምታ ውስጥ ያሉ
ለሥነ ልሳን፣ ለሥነ ጽሐፌ፣ ለታሪክ፣ ለባህልና ለማኅበራዊ ትስስር የሚጠቅሙ ሐሳቦች
ቢጠኑ የሚል የወፊፉት የምርምር ምክረ ሐሳቦች ተቀምጠውበታል።