Abstract:
ይህ ጥናት "የጅራፍ ግርፍርፊያ ጨዋታ ክዋኔ በቡሄ በዓል ማሳያነት" ምን እንደሚመስል
በመመርመር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በቡሄ በዓል ጅራፍ ግርፍርፊያ ጨዋታ የሚገጠሙ
ቃል ግጥሞችን ይዘት መተንተን፣ የቡሄ በዓል ጅራፍ ግርፍርፊያ ጨዋታ ፋይዳ ማሳየት
የሚሉ ናቸው። ከቀዳማይ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ውስጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምልከታና
የቡድን ውይይትን በመጠቀም ከመስክ መረጃ ተሰብቧል፡፡ ከመስክ የተገኙትን መረጃዎች
በመልክ በመልክ በማደራጀት አይነታዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በተግባራዊ፣ መዋቅራዊና
ክዋኔያዊ ንድፈ ሃሳቦች በመታገዝ በገለፃ መልክ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በጥናቱ ላይ የላይጋይንት
ወረዳ ማህበረሰብ የጅራፍ ግርፍርፊያ ጨዋታ ለማህበረሰቡ አካላዊ፣ ስነልቡናዊ እና
ሃይማኖታዊ ፋይደ እንዳለው ያስረዳል፡፡ ይህ ባህላዊ ጨዋታ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል
የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት፣ የወረዳው ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ሌሎች ማህበረ ባህላዊ ተቋማት
ትኩረት ቢያደርጉበት መልካም ነው።