Abstract:
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የአየር ንብረትና የልምላሜ ውበት ያጌጠች ፣ መጠነ-ሰፉ የኾነ ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ጥበብና አምልኮት
ያለባት ሀገር ናት፡፡ እነዘህም መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዲዮች የዋሸራ፣ የዋድላና የጎንጅ ቅኔዎች መፈጠሪያ ምንጮች ናቸው፡፡
የዘህ ጥናት ዋና ዒሊማ የዋሸራ፣ የዋድላና የጎንጅ ቅኔዎችን በንጽጽራዊ ጥናት ውስጣዊ ተመሳስሎቸውንና ሌዩነቶቻቸውን
ማጥናት ነው፡፡ አነሣሽ ምክንያቱ ሦስቱም ቅኔዎች በውስጣዊ ይዘታቸው መጠነ ሰፉ የሆኑ ልዩነቶችና ተመሳስልዎች
አሎቸው፡፡ እነዘህን ልዩነቶችና ተመሳስልዎች ለማዎቅ ብዙ መስዋትነት የሚጠይቅ በመሆኑ የሦስቱንም ቅኔዎች ምንነት ዛሬ
ላይ ያሉ ተተኪ ትውልዶች በቀላሉ እንዱያዉቁት ከመሻት የተነሣ ነው፡፡በተመረጠውም ርእስ ዙሪያ በጥናትና ምርምር ውስጥ
ያልተሠራበት መሆኑ ነው፡፡ ይህን ጥናታዊ ጽሐፌ ከግቡ ለማዴረስ በቅኔ ላይ የተጻፈ መጽሐፍችንና የተለያዩ የምርምር
ጽሐፍችን ከዋሸራ፣ ከዋድላና ከጎንጅ ቅኔዎች ንጽጽራዊ ጥናት ጋር ያላቸውን ተዛምዶ ለመመርመር በወሳኝ ናሙና
የአመራረጥ ዘዴ ውስጥ የሚገኘውን ዓላማ ተኮር አመራረጥ ዘዴን በመከተል ሰነድ ፍተሻ ተደርጎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም
በቅኔዎች ውስጥ ያለውን ምንነት በሰነድ ፌተሻ ከተገኙ መረጃዎች ጋር ለማረጋገጥ ከዋሸራ ቅኔ መምህራን መምህር
ጥዐመ ልሳንን፣ ከዋድላ ቅኔ መምህራን መምህር ቅደስንና ከጎንጅ መምህራን ደግሞ መምህር ሃይማኖትን በቃለ መጠይቁ
አሳትፋለች፡፡ ጥያቄዎችንም በአካል ተገኝቶ በጽሐፌ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠየቅና ውይይት በማዴረግ የቃለ መጠይቁ
ሥራ ተከናውኗል፡፡የጥናቱ ስልትም በዒይነታዊ አጠናን ስልት ውስጥ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በሰነድ ፍተሻና በቃለመጠይቅ የተገኙ
የሁልችንም ቅኔዎች ውስጣዊ ይዘታቸውን ለማነጻጸር ገላጭና ተራኪ የጥናት ምርምር መተንተኛ ዘዳዎችን በመጠቀም
የቅኔዎችን የርስ በርስ ተመሳስሎና ልዩነት በመረጃ መተንተኛ ዘዴ ውጤቱን ተንትኖ በማስረዳት ተብራርቶ ቀርቧሌ፡፡
በመጨረሻም የቅኔዎችን ንጽጽራዊ ጥናትን የጥናትና ምርምር አሠራርን በመከተል ሁሎችም ቅኔዎች ራሱን የቻለ ተመሳስል
አላቸው፡፡ ከእነዘህም የወቅታዊ ትርክታ፣የአስተምህሮ ባህል፣የቅኔዎች፣የአገባባት፣የስዋስው፣የአናቅጾች፣የዘሮችና የቤት መምቻ
ስንኞች አንድ መኾንና የመሳሰሉት ሲኾኑ፤ከልዩነታቸው ዙሪያ ደግሞ የቅኔ አጀማመር የአገባባት ሁኔታ፣ የቅኔ አጀማመር
የዚማ ልክ ሁኔታ፣የሐረግ አጠቃቀም ፣የነጂና የተነጂ አንቀጽና አገባባት ፣የዘርፍ አጠቃቀም ፣የአንቀጽ አጎላማሽ ሰዋስውን
አጠቃቀም ፣የዚማ ልክ ይዘት፣የተጸውኦ ስም አጠቃቀም፣በቅኔዎች ላይ የማይደረጉ ጸያፌ ቀለማት ዙሪያ ደግሞ አንዱ በቅኔ
ውስጥ አይሆንም ብሎ የደነገገውን አንደኛው ደግሞ ቅኔን የሚያስፈለስፍ ሕግ ሁኖ የሚያስቀኝበት ልዩነቶች ያለበት ጉዲዮች
ተገልጸው ጥናቱ ተጠንቶ የተገኘው ውጤትና ሊፈታ የታሰበውም ችግር መፌትሔ እንዲያገኝ ለሚመለከታቸው አካላት
የዋሸራ፣ የዋድላና የጎንጅ ቅኔዎች የሀገር ሀብት በመሆናቸው በቤተ መንግሥትና በትምህርት ምንስቴር እንክብካቤ
ቢደረግላቸው? በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች ቅኔዎችን በግእዛ ቋንቋ ውስጥ ጥናትና ምርምር
በጥልቀት እንዲደረግባቸው ቢደረግ? የቅኔ ጉባኤ ቤቶችና የመምህራን የሕይወት ታሪክም በጥንቃቄና በዘመናዊ መንገድ
ተሰብስቦ በቤተ መዘክርና በምርምር ተቋማት ውስጥ እንዲቀመጡ ቢደረግ? የሚሉና ሌሎችም የይሁንታ ሐሳቦች ተገልጸው ቀርበው የጥናትና ምርምሩ ፌጻሜ ሁኗ