Abstract:
ይህ ጥናት የገድለ ያሳይ የይዘት ትንተና በሚል ርእስ ላይ የተደረገ ሲኾን ጥናቱን ለማድረግ
አነሳሽ ምክንያቶችም ተመልክተዋል፡፡ በገድለ ያሳይ ዙሪያ በሳይንሳዊ መንገድ የተደረገ ጥናት
አጥኝው ባደረገው ኀሠሣ አለማግኘቱ፣ በአባ ያሳይ ዙሪያ የተጻፉ መረጃዎችም የሐሳብ ልዩነቶች
እንዳለሉቸው መገንዘቡ እና ገድሉ ቢጠና ለልዩነቶቹ መረጃ ተኮር ምላሽ እንደሚሰጥ ማሰቡ
ገድሉን ለማጥናት እንዳነሳሳው ተገልጧል፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ ገድለ ያሳይን በመተንተን
ያለውን ሥነ ጽሑፋዊ፣ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳ ማሳየት ሲኾንዓይነታዊ
የምርምር ዘዴን ተከትሎ መረጃዎችን በገላጭ የትንተና ሥልትን በመተንተን
ተከውኗል፡፡በአንድ በኩል አባ ያሳይ ኢትዮጵያዊ እንደኾነ፣ በሌላ መኩል ደግሞ በ18ኛው መቶ
ክፍለ ዘመን እንደነበረተደርጎ የተጻፈው መረጃ ትክክል አለመኾኑንይህ ጥናት መረጃን መሠረት
ያደረገ ምላሽለመስጠት ሞክሯል፡፡ ጥናቱ የገድልን ምንነት ከጽንሰ ሐሳብ አንጻር ያብራራ ሲኾን
በግእዝ ስለተጻፉ ገድላት ታሪካዊ ዳራ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ይህ ጥናት የገድለ ያሳይንአንድ
ቅጂ በመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭነት እንዲኹም ሌሎች ከገድለ ያሳይ ጋር ተዛማጅ የኾኑ
መጻሕፍትን፣መጽሔቶችን እና መጣጥፎችን ደግሞ በኹለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጭነት
ተጠቅሟል፡፡ በገድሉ ሥነ ጽሑፋዊ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳ ላይ ሰፊ
ትንተና ያደረገ ሲኾን በመጨረሻም ሌሎች ቅጆችን በማሰባሰብ በገድሉ ላይ የተመሳከረ
አርትኦት እና የትርጒም ሥራ ቢሠራበት፣ ተመራማሪዎች ይህን ጥናት እንደመነሻ ተጠቅመው
ክፍተቱን ቢሞሉ መልካም ይኾናል የሚሉ የይኹንታ ሐሳቦችን አስቀምጧል፡፡