Abstract:
ይህ ጥናት በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ የሚከወኑ የፎክሚዲያ አይነቶች እና ማንነት የመትከል
ሚናቸውን መመርመር የሚል ዋና ዓላማ ያለውና በዋና ዓላማው ውስጥም የታች አርማጭሆ
ማህበረሰብ በተደጋጋሚ የሚጠቀምባቸው የፎክሚዲያ አይነቶች ምን ምን ናቸው?፣የሃገረሰባዊ ተግባቦት
ዘዴዎቹ የሚከወኑባቸው አጋጣሚዎች ምንድን ናቸው?፣ በፎክሚዲያ የሚገልጸው የማህበረሰቡ ማንነት
ምንድን ነው? የሚሉት ንዑሳን ዓላማዎች በማድረግ ተካሄዷል፡፡ የጥናቱ ዓላማዎች ግባቸውን
እንዲመቱ ሲባልም ከካልዓይ የመረጃ ምንጮች በንባብ፣ከቀዳማዊ የመረጃ ምንጮች ደግሞ
በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ውይይት፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች በዓላማ ተኮር
የናሙና አመራረጥ ዘዴ ከተመረጡ 12 ተጠኝዎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎችን
በጥናቱ ዓላማ የተነሱ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በአግባቡ በማደራጀት በማደራጀት በመዋቅራዊ
ተግባራዊ ንድፈ ሃሳብ /Functionalist Structuralism Theory/፣በማህበራዊ ግንባታ ንድፈ ሃሳብ(Social
Constructionist theory) እንዲሁም በማንነትን ድፈሃሳብ (identity theory) ተተንትነዋል፡፡
ከትንታኔውም በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ በቃል ግጥሞች አማካኝነት፤ ማለትም በፉከራ፣ በሙሾና
በአዝማሪ ሀገረሰባዊ ሙዚቃ፤በቤተክርስቲያን ደወል እንዲሁም በሚልኪዎች፣ በምስጢራዊ ተግባቦትና
እንደ ጥሩምባ አይነት ድምጽ ባላቸው ቁሶች ውጤታማ ተግባቦት ይከወናል፡፡ ሰርግ፣ሰንበቴ፣ክርስትና
ለቅሶ የመከወኛ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ ተፈጥሯዊ ማንነቱን (አማራነቱን) ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና
ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ሆነው ማህበረሰቡ ማንነቱን በመትከል ረገድ ፎክሚዲያ ትልቅ ሚና አለው
ተጠቁሟል፡፡ የሚሉ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ከዚህ መነሻነት በትንታኔው የታች አርማጭሆ ማህበረሰብ
በተለያዩ የፎክሚዲያ አይነቶች የእርስ በርስ መስተጋብሩን ይከውናል፣የኑሮና የህይወት ፍልስፍናውን
ይፈክርበታል፣ መልካም ግንኙነታቸውን የሰመረ ያደርጉበታል፣ እንዲሁም ግጭቶችን ያበርዱበታል፡፡
በዚህም ደግሞ ዐበይት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ጨምሮ የጋራ እሴቶቻቸውን መጠበቅና
የባህላዊና ማህበራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ማንነትን መትከልና ማጠናከር የሚያስችል ተግባቦትና
የትብብር መረብ መዘርጋት ችለዋል፡፡ ከሚልመደምደሚያ ተደርሷል፡፡ ከመደምደሚያው በመነሳትም
በአካባቢው የሚከናወን ማንኛውም ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባር የማህበረሰቡን የተግባቦት
ባህል ግምት ውስጥ ያስገባ ቢሆን፣መንግስት ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በታች አርማጭሆ
የማህበረሰብ የተግባቦት ዘዴለስራ ዕቅዳቸው በማድረግ ቢንቀሳቀሱ፣የክልል፣ የዞንና የወረዳው አስተዳደር
እንዲሁም የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የፎክሚዲያ አይነትና እሴት
ለሌሎች ማሳወቅ ቢቻል፣የባህል ጥናት፣ የብዙሃን መገናኛና የሥነ ተግባቦት ተመራማሪዎች፣
ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ጥናት መነሻነት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ቢያደርጉ፣የታች አርማጭሆ ማህበረሰብ