BDU IR

የፎክሚዲያ አይነትና ማንነትን የመትከል ሚና በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ ለሁለተኛ ዲግሪ ከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥና

Show simple item record

dc.contributor.author በታደሰ ጸጋ
dc.date.accessioned 2021-04-23T11:19:17Z
dc.date.available 2021-04-23T11:19:17Z
dc.date.issued 2021-04-23
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12086
dc.description.abstract ይህ ጥናት በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ የሚከወኑ የፎክሚዲያ አይነቶች እና ማንነት የመትከል ሚናቸውን መመርመር የሚል ዋና ዓላማ ያለውና በዋና ዓላማው ውስጥም የታች አርማጭሆ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ የሚጠቀምባቸው የፎክሚዲያ አይነቶች ምን ምን ናቸው?፣የሃገረሰባዊ ተግባቦት ዘዴዎቹ የሚከወኑባቸው አጋጣሚዎች ምንድን ናቸው?፣ በፎክሚዲያ የሚገልጸው የማህበረሰቡ ማንነት ምንድን ነው? የሚሉት ንዑሳን ዓላማዎች በማድረግ ተካሄዷል፡፡ የጥናቱ ዓላማዎች ግባቸውን እንዲመቱ ሲባልም ከካልዓይ የመረጃ ምንጮች በንባብ፣ከቀዳማዊ የመረጃ ምንጮች ደግሞ በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ውይይት፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴ ከተመረጡ 12 ተጠኝዎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በጥናቱ ዓላማ የተነሱ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በአግባቡ በማደራጀት በማደራጀት በመዋቅራዊ ተግባራዊ ንድፈ ሃሳብ /Functionalist Structuralism Theory/፣በማህበራዊ ግንባታ ንድፈ ሃሳብ(Social Constructionist theory) እንዲሁም በማንነትን ድፈሃሳብ (identity theory) ተተንትነዋል፡፡ ከትንታኔውም በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ በቃል ግጥሞች አማካኝነት፤ ማለትም በፉከራ፣ በሙሾና በአዝማሪ ሀገረሰባዊ ሙዚቃ፤በቤተክርስቲያን ደወል እንዲሁም በሚልኪዎች፣ በምስጢራዊ ተግባቦትና እንደ ጥሩምባ አይነት ድምጽ ባላቸው ቁሶች ውጤታማ ተግባቦት ይከወናል፡፡ ሰርግ፣ሰንበቴ፣ክርስትና ለቅሶ የመከወኛ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ ተፈጥሯዊ ማንነቱን (አማራነቱን) ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ሆነው ማህበረሰቡ ማንነቱን በመትከል ረገድ ፎክሚዲያ ትልቅ ሚና አለው ተጠቁሟል፡፡ የሚሉ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ከዚህ መነሻነት በትንታኔው የታች አርማጭሆ ማህበረሰብ በተለያዩ የፎክሚዲያ አይነቶች የእርስ በርስ መስተጋብሩን ይከውናል፣የኑሮና የህይወት ፍልስፍናውን ይፈክርበታል፣ መልካም ግንኙነታቸውን የሰመረ ያደርጉበታል፣ እንዲሁም ግጭቶችን ያበርዱበታል፡፡ በዚህም ደግሞ ዐበይት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ጨምሮ የጋራ እሴቶቻቸውን መጠበቅና የባህላዊና ማህበራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ማንነትን መትከልና ማጠናከር የሚያስችል ተግባቦትና የትብብር መረብ መዘርጋት ችለዋል፡፡ ከሚልመደምደሚያ ተደርሷል፡፡ ከመደምደሚያው በመነሳትም በአካባቢው የሚከናወን ማንኛውም ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባር የማህበረሰቡን የተግባቦት ባህል ግምት ውስጥ ያስገባ ቢሆን፣መንግስት ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በታች አርማጭሆ የማህበረሰብ የተግባቦት ዘዴለስራ ዕቅዳቸው በማድረግ ቢንቀሳቀሱ፣የክልል፣ የዞንና የወረዳው አስተዳደር እንዲሁም የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የፎክሚዲያ አይነትና እሴት ለሌሎች ማሳወቅ ቢቻል፣የባህል ጥናት፣ የብዙሃን መገናኛና የሥነ ተግባቦት ተመራማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ጥናት መነሻነት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ቢያደርጉ፣የታች አርማጭሆ ማህበረሰብ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject ፎክሎር en_US
dc.title የፎክሚዲያ አይነትና ማንነትን የመትከል ሚና በታች አርማጭሆ ማህበረሰብ ለሁለተኛ ዲግሪ ከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥና en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record