Abstract:
አጠቃሎ
ይህ ጥናት የአቡነ ተጠምቀ መድኅንን የብራና ገድል ይዘት በመተንተን የተሠራ ነው፡፡ ዓቢይ ዓላማውም ይዘቱን በመተንተን ሁለንተናዊ ፋይዳውን ማሳየት ነው፡፡ ይህንንም ዓላማ ለማሳካት በዋና ነት የብራናውን ገድል ቀዳማይ ( የመጀመሪያ ) የመረጃ ምንጭ በማድረግ ሌሎች ኹለተኛ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም በዓይነታዊ የጥናት ዘዴ ትንተናው ተከናውኗል፡፡ ጥናቱ በአራት ምእራፎች የተከናወነ ሲኾን የመጀመሪያው ምእራፍ የጥናቱን ጠቅላላ መግቢያ በመያዝ ዳራውንና መነሻ ሐሳቡን፣ ዓላማውንና ጥቅሙን እንዲኹም ወሰኑንና ዘዴውን ይገልጻል፡፡ ምእራፍ ኹለት የብራናው ገድል የተገኘበትን ገዳም፣ የብራናው ገድል መሠ ረታዊ መረጃዎች፣ ስለ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ልደትና እድገት፣ ትምህርትና ክህነት፣ ምንኵስና ተአምራትና ቃል ኪዳን እንዲኹም እረፍት ይዘረዝራል፡፡ ምእራፍ ሦስት የጥናቱ ዋና ማዕከል ሲኾን የዓበይት ክስቶችና ድርጊቶች ጊዜያት፣ ዘይቤያዊ አነጋገሮች፣ የሐሳብ አወሳሰድ እና ልዩ ልዩ እሴቶች ከማስረጃዎች ጋር ተተንትነው ቀርበውበታል፡፡ የአቡነ ተጠምቀ መድኅን ገድል ለሀገርና ለማኅበረሰብ ያለው ኹለንተናዊ ጠቀ ሜታተጠቃልሎ የቀረበበት እና ለተጨማሪ ተግባራት ምክረ ሐሳብ የተጠቆመበት የጥናቱ መቋጫ ደግሞ ምእራፍ አራት ነው፡፡