dc.contributor.author | ፈቃዱ መስፍን | |
dc.date.accessioned | 2020-11-13T06:35:36Z | |
dc.date.available | 2020-11-13T06:35:36Z | |
dc.date.issued | 2020-11-13 | |
dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/11610 | |
dc.description.abstract | አኅጽሮተጽሑፍ ይህ ጥናት “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው” በሚል ርእስ ተመሥርቶ የተከናወነ ሲኾን ዐላማዉም ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች እና ምሁራን መጣጥፎች አንጻር ታየ በገለጸበት አግባብ የቃላት ሞኵሼነት ያለ ስለመኾን አለመኾኑ መመርመር ነው፡፡ ለዚህ ጥናት የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው መነሻ የተደረገው ከሌሎች ምሁራን ጽሑፎች በተለየ መልኩ ተመኵሳይያን ቃላት በተለይ በተለምዶ ሞኵሼ ተብለው የሚጠሩ ፊደላትን መሠረት በማድረግ በሰፊው መብራራታቸው ነው፡፡ ይህም በሌሎች ምሁራን ዘንድ እንዳለ መቀጠሉ ተለምዷዊ ሞኵሼ ፊደላት እውን ተመሳሳዮች ናቸውን በእነዚህ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላትስ ሞኵሼነትን ያሟላሉን የሚል ጥያቄ በመነሣቱ ነው ፡፡ የጥናቱ መረጃም የተሰበሰበው በዋናነት ሰነድ በመፈተሽ ሲኾን ምርመሩ ከዐይነታዊ የምርምር ዘውግ የሚመደብ እንደመኾኑ መጠን ገላጪ ንጽጽራዊ ዘዴን በመጠቀም ነው ማስረጃዎቹ የተተነተኑት፡፡ በጥናቱም ታየ ተለምዷዊ መኵሼ እየተባሉ የሚጠሩ ፊደላትን በዘፈቀደ እንደሚጠቀም እና ቃላት የተዋቀሩባቸው ፊደላት ቅርጻቸዉ ግምት ውስጥ ሳይገባ በድምፃቸዉ መመሳሰል ብቻ ተመኵሳይያን እንደሚባሉ እንዲሁም አዕማድ ግሶች ከተዋቀሩበት ፊደላት መለያየት በተጨማሪ የተለየ ትርጕም ሳይኖራቸውና የአድራጊነትን፣ የተደራጊነትንና የአስደራጊነትን ቅርጽ ሳያሟሉ ተመኵሳይያን የሚባሉ መኾናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከአንድ የግስ ሥር በርባታ የተገኙ እና በርባታቸዉ ምክንያት የተለያየ ፆታ፣ መደብና ቁጥር የሚገልጹ ኾነው በንባብ በመመሳሰላቸው ቃላት ሞኵሼዎች የተባሉ ስለመኾናቸውም ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናት በቅርጽ እንጅ በድምፅ የማንለያቸውን ፊደላት ድምፃቸዉን መልሶ ለማገኘት እንደመነሻ ኾኖ እንደሚያገለግል እና በምሁራኑ ዘንድም ስሕተትን ከማረም ጀምሮ ለተጨማሪ ጥናት መነቃቃትን በመፍጠር በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Geʽez | en_US |
dc.title | ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |