BDU IR
ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው
Login
BDU IR Home
→
Faculty of Humanities
→
Geʽez
→
Thesis and Dissertations
→
View Item
JavaScript is disabled for your browser. Some features of this site may not work without it.
ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው
ፈቃዱ መስፍን
URI:
http://hdl.handle.net/123456789/11610
Date:
2020-11-13
Abstract:
አኅጽሮተጽሑፍ ይህ ጥናት “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው” በሚል ርእስ ተመሥርቶ የተከናወነ ሲኾን ዐላማዉም ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች እና ምሁራን መጣጥፎች አንጻር ታየ በገለጸበት አግባብ የቃላት ሞኵሼነት ያለ ስለመኾን አለመኾኑ መመርመር ነው፡፡ ለዚህ ጥናት የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው መነሻ የተደረገው ከሌሎች ምሁራን ጽሑፎች በተለየ መልኩ ተመኵሳይያን ቃላት በተለይ በተለምዶ ሞኵሼ ተብለው የሚጠሩ ፊደላትን መሠረት በማድረግ በሰፊው መብራራታቸው ነው፡፡ ይህም በሌሎች ምሁራን ዘንድ እንዳለ መቀጠሉ ተለምዷዊ ሞኵሼ ፊደላት እውን ተመሳሳዮች ናቸውን በእነዚህ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላትስ ሞኵሼነትን ያሟላሉን የሚል ጥያቄ በመነሣቱ ነው ፡፡ የጥናቱ መረጃም የተሰበሰበው በዋናነት ሰነድ በመፈተሽ ሲኾን ምርመሩ ከዐይነታዊ የምርምር ዘውግ የሚመደብ እንደመኾኑ መጠን ገላጪ ንጽጽራዊ ዘዴን በመጠቀም ነው ማስረጃዎቹ የተተነተኑት፡፡ በጥናቱም ታየ ተለምዷዊ መኵሼ እየተባሉ የሚጠሩ ፊደላትን በዘፈቀደ እንደሚጠቀም እና ቃላት የተዋቀሩባቸው ፊደላት ቅርጻቸዉ ግምት ውስጥ ሳይገባ በድምፃቸዉ መመሳሰል ብቻ ተመኵሳይያን እንደሚባሉ እንዲሁም አዕማድ ግሶች ከተዋቀሩበት ፊደላት መለያየት በተጨማሪ የተለየ ትርጕም ሳይኖራቸውና የአድራጊነትን፣ የተደራጊነትንና የአስደራጊነትን ቅርጽ ሳያሟሉ ተመኵሳይያን የሚባሉ መኾናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከአንድ የግስ ሥር በርባታ የተገኙ እና በርባታቸዉ ምክንያት የተለያየ ፆታ፣ መደብና ቁጥር የሚገልጹ ኾነው በንባብ በመመሳሰላቸው ቃላት ሞኵሼዎች የተባሉ ስለመኾናቸውም ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናት በቅርጽ እንጅ በድምፅ የማንለያቸውን ፊደላት ድምፃቸዉን መልሶ ለማገኘት እንደመነሻ ኾኖ እንደሚያገለግል እና በምሁራኑ ዘንድም ስሕተትን ከማረም ጀምሮ ለተጨማሪ ጥናት መነቃቃትን በመፍጠር በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡
Show full item record
Files in this item
Name:
FeqaduMesfin (2).pdf
Size:
888.5Kb
Format:
PDF
View/
Open
This item appears in the following Collection(s)
Thesis and Dissertations
Search
Search
This Collection
Browse / Search
All of BDU IR
Institute, Faculity, School, college and its Collections
By Issue Date
Authors
Titles
Subjects
By Submit Date
This Collection
By Issue Date
Authors
Titles
Subjects
By Submit Date
My Account
Login
Register
Statistics
View Usage Statistics