Abstract:
የመጀመሪያው ክፍል የትርጉም ሥነ ጽሑፍ የታየበት፤ የሠለጠነው ዓለም ሃይማኖት ክርስትና ይበልጡን የጎላበት ፣ ኢትዮጵያ የክርስትና ሐይማኖትን የተቀበለችበት እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥልጣኔ ዘመን እንደነበር እንረዳለን፡፡ በመሆኑም ሥልጣኔው ከሐይማኖት ጋር ተዋህደው በሃገሪቱ ላይአብዛኛው ጽሑፎች ሐይማኖትን የሚመለከቱ እንደነበሩ መረዳት ይቻላል፡፡
ሁለተኛው ከሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ያለው ጊዜ ደግሞ፣ ከሐይማኖት ውጭ ጭምር ልዩ ልዩ መልክ ያለውና የተለየም የእድገት ደረጃ ያሳየበት የሥነ ጽሑፍ መልኩም ከባህል፣ ከፖለቲካ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከፍልስፍና፣ ከማህበራዊ ወዘተ አንፃር እድገት ያሳየበት ነው፡፡
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ በዓለም ካሉት ሀገራትም የራስዋ ባህል፣ ቅርስ እና ጥንታዊ ቀደምት ሥልጣኔ ሀገራት ውስጥ አንዷ መሆኗን አበበ /2008፡1/ እንደሚከተለው ገልፆታል፡፡