| dc.contributor.author | ተዋበ, ሞስዬ | |
| dc.date.accessioned | 2026-06-05T08:14:46Z | |
| dc.date.available | 2026-06-05T08:14:46Z | |
| dc.date.issued | 2017 | |
| dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/16872 | |
| dc.description.abstract | ይህ ጥናት ፍጹም አማርኛ የመስሉትን ጥቂት የግእዝ ቃላትን መተንተን እና ማስተዋወቅ በሚል ርእስ ተመሥርቶ የተከናወነ ሲሆን አነሣሽ ምክንያቱ በተለምዶ የግእዝ ቃላትን የአማርኛ ቃላት አስመስሎ የመረዳት ባኅሪ በማኅበረሰቡ ዘንድ ይስተዋላል፡፡እንዲሁም የግእዝ ቋንቋ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ መነገሩ እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር ተየይዞ ጨርሶ እንደሞተ ቋንቋ ተደርጎ በመወሰዱ ነው ፡፡ ዐላማውም በግእዝ፣በአማረኛ መጻሕፍት እና በምሁራን መጣጥፎች እነዚህ ፍጹም አማርኛ የመሰሉ የግእዝ ቃላትን መፈለግ፤መኖራቸውን እና አለመኖራቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ምርምሩ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ መረጃ የተሰበሰበው በዋናነት ሰነድ በመፈተሽ ሲኾን ለሙያው ቅርብ የኾኑ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ በመጠየቅ ተጨማሪ ሐሳብ ወስዷል፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ፍጹም አማርኛ የመሰሉ የግእዝ ቃላት መኖር እና አለመኖራቸውን በመሠረታዊነት ማረጋገጥ እንዲቻል ነው፡፡ እንደዚሁም እነዚህ የሚፈለጉ ቃላት በተጨባጭ እንዳሉ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ አጥኝዉ ሰነድ ፍተሻ ሲያደርግ በየቅኔ ቤቱ የሚገኙ የግስና የአገባብ መጻሕፍትን ፍጹም አማርኛ የመሰሉ የግእዝ ቃላት እንዳሉት ተመልክቷል፡፡ የጥናቱ ውጤት ላንባቢያን ግልጥ ይሆን ዘንድ በዘር አወጣጥ ምደባ እና በቅርፀ ፊደል ልየታ እንዲሁም የግእዝ ቋንቋ ቃላትን በመለየት ፍጹም አማረኛ የመሰሉትን የግእዝ ቃላት እንዳሉ ተመላክቷል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናት ፍጹም አማረኛ የመሰሉ የግእዝ ቃላት በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የተገኙ እንደሆነ እና ጥናት እና ምርምር ለማድረግ ለሚፈልግ ተመራማሪ ቁጥራቸው ያልተገደበ በመኾኑ ለዠደፊት ለተጨማሪ ጥናት መነቃቃትን በመፍጠር በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en_US | en_US |
| dc.subject | Geʽez | en_US |
| dc.title | ፍጹም አማርኛ የመስሉትን ጥቂት የግእዝ ቃላትን ማስተዋወቅ | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |