BDU IR

የይዘት ትንተና በገድለ አብርሀ ወአጽብሐ

Show simple item record

dc.contributor.author ፈንታሁን, ደሴ
dc.date.accessioned 2025-08-05T06:21:41Z
dc.date.available 2025-08-05T06:21:41Z
dc.date.issued 2017-02
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/16830
dc.description.abstract ይህ ጥናት የገድለ አብርሀ ወአጽብሐ የይዘት ትንተና በሚል ርእስ ላይ የተሠራ ሲኾን ጥናቱን ለመሥራት አነሣሽ ምክንያቶችም ተመላክተዋል፡፡ ቅዱሳን ነገሥት አብርሀ ወአጽብሐ በስማቸው ትምህርት ቤት የተሠራላቸው፣ በቤተክርስቲያን በዓል የሚከበርላቸው ምን ቢሠሩ ነው ? የሚል ጥያቄ አጥኚዉ ስለነበረው ገድሉን ለማጥናት እንደ አነሳሳው ተገልጧል ፡፡ ዐቢይ ዐላማውም ገድለ አብርሀ ወአጽብሐን በመተንተን አብርሀ ወአጽብሐ እነማን ነበሩ፣ ያላቸውን ታሪካዊ፣ ስነ ጽሑፋዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳ ማሳየት ሲኾን ዐይነታዊ የምርምር ዘዴን ተከትሎ መረጃዎችን በገላጭ የትንተና ሥልት በመተንተን ተከውኗል ፡፡ ይህንንም ዐላማ ለማሳካት በዋናነት አንድ የብራናዉን ገድል ቅጅ ቀዳማይ የመረጃ ምንጭ በማድረግ የተጠቀመ ሲኾን፤ ሌሎች ከገድለ አብርሀ ወአጽብሐ ጋር ዝምድና ያላቸው ወይም ስለ ገድሉ ተጨማሪ መረጃ የሰጡ መጻሕፍት፤ መጽሔቶች፣ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደ ኹለተኛየመረጃ ምንጭ ተጠቅሟል፡፡ ይህም ጥናት በዓይነታዊ የጥናት ዘዴ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ ጥናቱ የገድልን ምንነት ከፅንሰ ሐሳብ አንጻር ያብራራ ሲኾን በግእዝ ስለተጻፉ ገድላት ታሪካዊ ዳራ ማብራሪያ ሰጥቷል ፡፡ በገድሉ ስነ ጽሑፋዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳ ላይ ሰፊ ትንተና ያደረገ ሲኾን በመጨረሻም ሌሎች ቅጆችን በማሰባሰብ በገድሉ ላይ የተመሳከረ አርትዖት እና የትርጒም ሥራ ቢሠራበት፣ ተመራማሪዎች ይህን ጥናት እንደመነሻ ተጠቅመው ክፍተቱን ቢሞሉ መልካም ይኾናል የሚሉ የይኹንታ ሐሳቦችን አስቀምጧል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Geʽez en_US
dc.title የይዘት ትንተና በገድለ አብርሀ ወአጽብሐ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record