dc.contributor.author | አሰፋ, ታፈረ | |
dc.date.accessioned | 2024-03-12T07:58:43Z | |
dc.date.available | 2024-03-12T07:58:43Z | |
dc.date.issued | 2015-06 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15695 | |
dc.description.abstract | የእጅ ጽሑፎች ከተሰበሰቡ በኋላ መዘርዝር ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስብስቡ በራሱ የእጅ ጽሑፉን ሙሉ ታሪክ ሊነግረን አይችልምና። መዘርዝር ግን የመጻፉን ዝርዝር እና ትክክለኛ መግለጫ፤ የተሟላ እና አጭር የእጅ ጽሑፍ ታሪክን ያቀርባል፡፡ ቢኾንም በዋደና ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብራና ላይ በግእዝ ቋንቋ ተጽፈው የሚገኙት የእጅ ጽሑፎች መዘርዝር ያልተሰራላቸው ሲኾን የዚህ ጥናት ዋና ዓላማም በአማራ ክልል በአዊ ዞን ሀገረ ስብከት በባንጃ ወረዳ በኳችኳች ዋደና ቀበሌ በሚገኘው በዋደና ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብራና ላይ በግእዝ ቋንቋ በተጻፉ 12 የእጅ ጽሑፎች መዘርዝር ማዘጋጀት ነው፡፡ይህንን አላማ ለማሳካት ተግባራዊ የኾነው የምርምር ዘዴ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት ይህ ጥናት በቋንቋ አማካኝነት በቃላት የሚቀርብ ሲኾን የመጻሕፍቱን መረጃ ከውጫዊ እስከ ውስጣዊው ክፍል ዘርዝሮ ስለሚያቀርብ ነው ፡፡ በዋናነት መዘርዝር የሚሰራባቸው የዋደና ተክለሃይማኖት የእጅ ጽሑፎች ሲኾኑ ተዛማጅነት ያላቸው መዛግብቶችንም እንደ ኹለተኛ መረጃ አድርጎ ተጠቅሟል፡፡ ጥናቱ ከፅንሰ ሐሳብ አንፃር የመዘርዝርን ምንነት አስረድቷል፡፡ መጻሕፍቱን በዝርዘር አሳውቃል፡፡ በተጨማሪም የተዘረዘሩ መጻሕፍትን የተሰሩበን ቁስ አካል፤ የመጻሕፍቱን የአቀማመጥ ኹኔታ፤ የመጻሕፍቱን ውስጣዊ ይዘት እና መጻሕፍቱ የተጻፉበትን ወይም የተገለበጡበትን ዘመን በጥልቀት በመመርመር መዘርዝር አድርጓል፡፡ ይህን ጥናት እንደ ግብአት በመጠቀም ገና ጥናት ያልተደረገባቸው በገዳማት፣በአድባራት እና በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ብዙ የብራና መጻሕፍት ሊገኙ ስለሚችሉ አጥኝዎች እና ተመራማሪዎች ለዚህ ዘርፍ ትኩረት ቢሰጡ የብራና መጻሕፍት እንዳይጎዱ ይሆናል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Geʽez → | en_US |
dc.title | በአዊ ዞን የሚገኘው የዋደና ተክለ ሃይማኖት የእጅ ጽሑፎች መዘርዝር | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |