dc.contributor.author | በመልአኩ, ታረቀኝ | |
dc.date.accessioned | 2023-07-21T08:00:41Z | |
dc.date.available | 2023-07-21T08:00:41Z | |
dc.date.issued | 2015-06 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15513 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናታዊ ጽሐፍ ትኩረቱ በገድለ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ ላይ ሲኾን ዋና ዒላማዉም የገድሉን ይዘት መተንተን ነው፡፡ ለጥናቱ የተመረጠዉ የብራና ገድልም የተገኘው በደብረ ባሕርይ ጋሥጫ አባ ጊዮርጊስ እና አባ በጸሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም ነው፡፡ የጥናቱ ዳራ፣ አነሣሽ ምክንያት፣ ዋና እና ዝርዝር ዒላማዎች፣ ጥናቱ የመለሳቸዉ ጥያቄዎች፣ የጥናቱ ጠቀሜታ፣ ወሰኑ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሔዎች በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ስለገድል ምንነት፣ ክፍሎች፣ የተጻፉባቸው ቋንቋዎች እና ዒይነቶች በክለሣ ድርሳናት ሥር የቀረቡ ሲኾን ጥናቱም ዒይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴን በተመለከተም ሰነድ ፍተሻ፣ ፎቶ ካሜራ እና ቃለመጠይቅ ናቸው፡፡ ለትንተናዉም ገላጭ ስልትን በመገልገል ትረካዊ እና ተግባራዊ ንድፈ–ሐሳቦችም ጥቅም ላይ ዉለዋል፡፡ በጥናቱም ገድለ በጸሎተ ሚካኤል የተገኘበት ቦታ እና የገድሉ ጸሓፊ ስም እንዱሁም የገድሉ ውጫዊ እና ውስጣዊ መገለጫዎች ተካተዉ የተገለጹ እና ገድሉም ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነምግባራዊ ይዘቶች እንዳሉት ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም የአባ በጸሎተ ሚካኤል ታሪክ እና አስተዋጽኦ፣ ገድሉ ከሌሎች መጻሕፍት የጥቅስ አወሳሰድ እና የቋንቋ አጠቃቀም ስልት በጥናቱ የተዳሰሱ ሲኾን በገድሉ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ሰዎች እና ቦታዎችም በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ የጥናቱ ማጠቃለያ እና የይኹንታ ሐሳብም ተካተዉ ቀርበዋል፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Geʽez | en_US |
dc.title | ይዘት ትንተና በገድለ በጸሎተ ሚካኤል | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |