dc.contributor.author | ፍሬቃል, ዳምጤ | |
dc.date.accessioned | 2023-06-05T12:23:07Z | |
dc.date.available | 2023-06-05T12:23:07Z | |
dc.date.issued | 2015-02 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15337 | |
dc.description.abstract | የጥናቱ ዋና ዐላማ የክዑባን ፊደላትን ሰዋስዋዊ ባሕርያት የግስ ርባታቸዉ፣ የዘር አወጣጣቸዉ ምን እንደሚመስል መተንተን ሲኾን አጥኚዉን ለምርምር ሥራ የገፋፉት ዐበይት ምክያቶች ደግሞ በግእዝ ቋንቋ መዛግብተ ቃላት፣ የግእዝ መጻሕፍት ውስጥ ሥርዐተ ጽሕፈታቸዉ እና ሰዋስዋዊ አገባባቸዉ ከትናጋ ፊደል ጋር እየተቀላለቀለ ሲጻፈ መታየታቸው፣ መካነ ፍጥረታቸዉና ባሕርየ ፍጥረታቸዉ በግልጽ ባለመለየቱ፣ የመዋዋሳቸዉ ጉዲይ እስከ ምን ድረስ እንደ ኾነ ተብራርቶ ባለመቀመጡ፣ ለቅኔ ቤት መምቻ ሲኾን ቤት ሲያፈልሱ መታየታቸዉ ነው፡፡ ጥናቱ ከግብ እንዲደርስ ዐይነታዊ የምርምር ዘዱን በመጠቀም መረጃዎቹ በሰነድ ፍተሻ እና ቃለመጠይቅ ከተሰበሰቡ በኋላ ዐላማ ተኮር ንሞናን በመተግበር መረጃዎቹ በገላጭ የመረጃ መተንተኛ መንገድ ተብራርተው ቀርበዋል፡፡ በጥናቱም የክዑባን ፊደላት ስያሜዎቻቸዉ ምን ምን እንደኾኑ፣ ከእናት ፊደላት የሚዋሱባቸዉ መንገዶች፣ የአማርያን ተውላጣተ አስማት ሰዋስዋዊ ባሕርያት፣ በቅኔ ቤት መምቻኌት ምን እንደሚመስሉ፣ የዘር አወጣጥ እና ግስ አመሠራረት እንዲዂም መካነ ፍጥረታቸዉ እና ባሕርየ ፍጥረታቸዉ እንዴት እንደኾኑ ትንተና ተደርጎባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በዘህ ጥናት ክዑባን ፊደላት በመካነ ፍጥረታቸዉ የከንፈር ትናጋ ሲኾን በአንዳንድ መንገድ ደግሞ ካዕብ እና ሳብዕ ሆሄያትን ከትናጋ ፊደላት እንደሚዋሱ፣ የራሳቸዉ የኾነ ዘር አወጣጥ ያላቸው እና አዲስ ዘር ሲገኝም አዲስ ግስ መመሥረት እንደተቻለ ጥናቱ ያሳያል፡፡ በጥናት ግኝቱም ፊደላቱ የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው መኾኑ፣ እያቀላቀሉ የቅኔ ቤት መምቻ ማድረግ እንደማይቻል፣ ትናጋውያን ምሉአን ስለኾን ከክዑባን ፈጽሞ እንደማይዋሱ ታይቷል፡፡ በዘህም መሠረት የራሳቸው ትርጉም ያለው ቀመረ ፊደል ቢወጣላቸው፣ ርስ በርስ ከመወዛገብ የራሳቸዉ ግስ፣ ነባር፣ መዝገበ ቃላት እን አልፋ ቤት ተዘጋጅቶላቸው ወጥ አካሔድ እንዲኖራቸው ቢደረግ ግኝቱ ጥቆማ ይሰጣል፡፡ ቊልፍ ቃላት፡- ክዑባን ፣ ቅኝት፣ ፊደል፣ ሰዋስው፣ ክዑባን እና ባሕርያት ፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Geʽez | en_US |
dc.title | የክዑባን ፊደላት ሰዋስዋዊ ባሕርያት ቅኝት በተመረጡ የግእዝ መጻሕፍት | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |