BDU IR

"ተከታታይነትና ለውጥ በቦታ ስያሜዎች ላይ በደሴ ከተማ ተተኳሪነት"

Show simple item record

dc.contributor.author ሀያት ፈንታሁን
dc.date.accessioned 2023-05-03T13:17:49Z
dc.date.available 2023-05-03T13:17:49Z
dc.date.issued 2015-02
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15233
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በደሴ ከተማ የሚገኙ የቦታ ስሞችን ተከታታይነትና ለውጥ መመርመር ሆኖ ተከታታይነትን ጠብቀው የሚገኙ ቦታዎችን ስያሜዎች መፈተሽ፤ የቦታ ስሞች ለውጥና የለውጥ ምክንያቶችን መለየት፤ የቦታ ስሞችን ፋይዳ መለየት፤ የቦታ ስሞቹ ተከታታይነትና ለውጥ ላይ ማህበረሰቡ ያለውን አመለካከት መፈተሸ የሚሉ ዝርዝር ዓላማዎችን አካትቷል፡፡ ጥናቱን ከግብ ለማድረስ የተለያዩ መረጃዎች ከመስክ እና ከተለያዩ ሰነዶች ተሰብስበዋል፡፡ ጥቅም ላይ የዋሉት የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም፤ ቃለመጠይቅ፣ ሰነድ ፍተሻ፣ ምልከታ እና ቡድን ተኮር ዉይይት ናቸዉ፡፡ ጠቋሚ ናሙናን በመጠቀም ለጥናቱ በመረጃ አቀባይነት የተሳተፉ 21 መረጃ አቀባዮች ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ በተመረጠዉ ደሴ ከተማ የሚገኙ የቦታ ስያሜዎችን ሁሉንም በመዉሰድ ከእነዛ ዉስጥ በእጣ ንሙና የተመረጡት የቦታ ስሞች ለትንተና ቀርበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎችም በተግባራዊ ንድፈ ሀሳብ እና በስነፍቻዊ ንድፈ ሀሳብ መሰረት ተተንትነዉ በገላጭ እና አይነታዊ የትንተና ዘዴ ተብራርተዉ ቀርበዋል፡፡ ከመረጃ ትንተናዉም የቦታ ስያሜ መነሻ ምክኒያቶች እና የቦታ ስያሜ የለውጥ ምክንያቶች የማህበረሰቡ ገጠመኝ፣ የሀይማኖት ተቋማት መስፋፋት፣ ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ የመሰረተ ልማት መስፋፋት፣ የንግድ እንቅስቃሴ ወዘተ ሲሆኑ የለውጡ ሰበቦች ደግሞ የፖለቲካዊ ሥርዓት ለውጥ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ስነልቡናዊ ሁኔታዎች መሆናቸውን መለየት ተችሏል፤ በተለወጡ የቦታ ስሞች ላይም የማህበረሰቡ አመለካከት አወንታዊ ስለመሆኑ በመረጃ ትንተና በተገኘው ውጤት ተረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ ብዙዎቹ የቦታ ስሞች ተከታታይነትን ጠብቀው ለመዝለቃቸው ምክንያቶቹ በማህበረሰቡ ማህበራዊ ህይወት፣ ማንነትና ስነልቡና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ትርጓሜና አንድምታ የሌላቸው ከመሆኑ ጋር ሊያያዙ እንደሚችሉ መረጃዎች አመላክተዋል። en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title "ተከታታይነትና ለውጥ በቦታ ስያሜዎች ላይ በደሴ ከተማ ተተኳሪነት" en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record