BDU IR

የሽውዬ እና ምሻምሾ ባህላዊ ጨዋታ ክዋኔ እና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ ማህበረሰብ

Show simple item record

dc.contributor.author ሰላማዊት, ጌታሁን
dc.date.accessioned 2022-11-23T08:37:53Z
dc.date.available 2022-11-23T08:37:53Z
dc.date.issued 2014-08
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14533
dc.description.abstract አጠቃሎ ይህ ጥናት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ በሚከበረው የሽውዬ እና ምሻምሾ ባህላዊ ጨዋታ ክዋኔ እና ፋይዳ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ። ጨዋታው በአማርኛ ዥዋዥዌ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በኽምጣጛ ቋንቋ ወይም በመገኛ ቋንቋው እሽውዬ ተብሎ ይጠራል ፡፡ስለሆነም እኔም በመገኛው ቋንቋ ያለውን እሽውዬ የሚለውን ስያሜ ጥናቴ ላይ ተጠቅሜበት አለሁ፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማው ደግሞ ክዋኔና ፋይዳውን መመርመር ነው ፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳት ትኩረት የተሰጠው ጨዋታው ያለውን የክዋኔ ሂደትና ጨዋታው የሚያበረክተውን ፋይዳዎች የሚያሳዩ የምርምር ጥያቄዎችን በማዘጋጀት በምልከታ ፣በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ የቡድን ውይይት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም መረጃው ከመስክ ተሰብስቧል ፡፡ በዚህም መሠረት በዝቋላ ወረዳ የሽውዬ እና ምሻምሾ ባህላዊ ጨዋታ ክብረ በዓል ወቅት ከክበረ በዓሉ ጅማሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ ያለውን ክዋኔ ሲከውኑ የሚገጠሙ የቃል ግጥሞችን ፋይዳዎችን በየወገናቸው በመመደብ ተተንትነዋል፡፡ በዚህ ጥናት ማህበረሰቡ በክዋኔዎች አማካይነት በቀጥታና በጎንዮሽ ሃሳቡን በመግለፅ ሲያስተምሩበት፣ ሲመክሩበት፣ ሲያዝናኑበት፣ ሲያስተላልፉበትና ባህላዊ ማንነትቱን ሲያስጠብቁበት መቆየቱን ማረጋገጥ ተችሏል። ትንታኔ የተደረገው በዋናነት መረጃዎቹ ከተሰበሰቡበት አውድ አኳያ የይዘት ትንተና የተጠቀመ ሲሆን ክዋኔው በማህበረሰቡ ውስጥ ካለቸው ፋይዳ አንጻር ደግሞ የክውና ንድፍ ሃሳብን፣ የቁሶችን ውክልና እና ተግባራዊ ንድፍን ሃሳብን መሠረት ያደረገ ነው። በክዋኔው አማካይነት የሚተላለፉ ቁምነገሮች እና የሚከወኑ ክዋኔዎች የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ መስተጋብር የማስተማር ሚና እንዳላቸው የጥናቱ ውጤት ያሳያል። በመሆኑም ለወጣቱ ትውልድ ማስተማርያነት ማዋል እንደሚቻል በጥናቱ መደምደሚያ እና ይሁንታ ውስጥ በዝርዝር ተገልጸዋል። en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title የሽውዬ እና ምሻምሾ ባህላዊ ጨዋታ ክዋኔ እና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ ማህበረሰብ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record