BDU IR

ፈጫሳን እንደ ህይወት ዑደት ማስጠበቂያ ስርዓት በግራር ጃርሶ ወረዳ ማህበረሰብ

Show simple item record

dc.contributor.author በእድላም, ንጉሴ
dc.date.accessioned 2022-08-31T11:57:34Z
dc.date.available 2022-08-31T11:57:34Z
dc.date.issued 2011-06
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14071
dc.description.abstract ይህ ጥናት የግራር ጃርሶ ወረዳ ማህበረሰብ ፈጫሳን እንደ ህይወት ዑደት ማስጠበቂያ ስርዓት የተጠቀመበት ሁኔታ መመርመር የሚል አብይ አላማ ያለው ሲሆን ለዚህ አላማ ከግብ መድረስ ደግሞ በስርዓተ ከበራው አጀማመር (ሚቱ) እና በስርዓተ ከበራው መካከል ያለውን ግንኙነት መመርመር፣ በክዋኔው ውስጥ ያሉ ልማዶችና ልማዶችን ለመከወን አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሶች በማህበረሰቡ ህይወት ውስጥ ያላቸውን ፋይዳ ማስረዳት እንዲሁም በስርዓተ ከበራው ክዋኔ ወቅት የሚከወኑ ሃገረሰባዊ ሙዚቃዎች ቃል ግጥሞች ይዘት በመመርመር የማህበረሰቡን ሕይወት ከማስጠበቅ አንጻር ያላቸውን ፋይዳ መፈተሸ የሚሉ ዝርዝር አላማዎች የተመረመሩበት ነው፡፡ ጥናቱ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ሲሆን በጥናቱ ለመረጃ አቀባይነት የተሳተፉ ሰዎችም በአላማ ተኮር እና ጠቋሚ የናሙና አመራረጥ ዘዴዎች ተመርጠዋል፡፡ የመስክ መረጃዎች በምልከታ፣ ቃለመጠይቅ እና ተተኳሪ ቡድን ውይይት በመታገዝ የተሰበሰቡ ሲሆን በሚት ሪችዋል ቲዎሪ የመረጃ መቀንበቢያነት በገለጻ እና የይዘት ትንተና ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡ ከትንታኔውም በተገኘው ሃሳብ መሰረት ፈጫሳ ስርዓተ ከበራ ተጠኚው ማህበረሰብ ድሮ ብሎ በሚጠራው ጊዜ የኖረች አንዲት የማህበረሰቡ አባል ልጅ ያለመውለድ ችግር ገጥሟት ይህን ችግር ላስወገደችላት አማልክት አሷ እና እንደሷ አይነት ችግር የገጠማቸው የማህበረሰቡ አባላት ችግራቸው ይፈታላቸው ዘንድ እንዲከውኑት በታዘዙት መሰረት የግራር ጃርሶ ወረዳ ማህበረሰብም ዛሬ ድረስ በህይወት ሲኖር ባለታሪኳ የደረሳትን በረከት ያገኝ ዘንድ፣ ለመኖሩ እንቅፋት የሚሆኑ ችግሮች እንዳይከሰቱበት አስቀድሞ ለመከላከል እና የተከሰቱበትን ችግሮችንም ለማስወገድ ሲል ለአማልክቷ ልመና እና ምስጋና የሚያቀርብበት ስርዓታዊ ከበራ ነው፡፡ የዚህ ስርዓተ ከበራ ክዋኔ ከአጀማመሩ ወይም ከሚቱ ጋር ዝምድና ያለው እና መንፈሷን ከመለመን ውጭ ደግሞ በተወሰኑ ስርዓቶች የተለየ ነው፡፡ በፈጫሳ ስርዓተ ከበራ ላይ የሚከወኑ ስርዓታዊ ልማዶች ዘር ለመተካት፣ ለከብቶችን እርባታ፣ ለሰብል ዕድገት፣ ማህበራዊ ትስስርን ለመፍጠር፣ ሰላም፣ ጤናንና በረከትን ለማግኘት እና ወደተሻለ ኑሮ ለመሸጋገር በማገልገል የማህበረሰቡን የህይወት ዑደት ማስጠበቂያ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በስርዓተ ከበራው ላይ የሚከወኑ ሃገረሰባዊ ሙዚቃዎች ቃል ግጥሞች እና በተለያዩ ልማዶች ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ቁሶች ማህበረሰቡ ስርዓተ ከበራውን ለሚከውንላት አማልክት ለመለመኛናነት ለማመስገኛንት በመጠቀም ሕይወቱን ለማስጠበቅ የሚገለገልባቸው ናቸው፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title ፈጫሳን እንደ ህይወት ዑደት ማስጠበቂያ ስርዓት በግራር ጃርሶ ወረዳ ማህበረሰብ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record