Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የአድአ በርጋ ወረዳ ማህበረሰብ የዛፍ እሳቤ እና ፋይዳ ምን
እንደሚመስል መመርመር ሲሆን ዓይነታዊ ምርምርን መሰረት በማድረግ የመስክ መረጃዎች
በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በቡድን ተኮር ውይይት በመታገዝ ተሰብስበዋል። የጥናቱ ተሳታፊ
ሰዎች የተመረጡት በዋናነት በዓላማ ተኮርና ጠቋሚ የናሙና ስልት ነው። በዚህ ጥናት
በማህበረሰቡ ዉስጥ ክብር የሚሰጣቸውን 5 ዋና ዋና የዛፍ ዓይነቶችን በመጥቀስ ዛፍ
በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን እሳቤ እንዲሁም ፋይዳ ለማሳየት ጥረት ተደርጓል። መረጃዎቹ
ተፈጥሯዊ እና ኢ ተፈጥሯዊ መቼቶችን በመጠቀም የተሰበሰቡ ሲሆን በገላጭ የመረጃ
መተንተኛ ዘዴ የተተነተኑ በጽንሰ ሀሳቦችና ቀድመዉ ከተገኙ መረጃዎች ጋር በማገናኘት
በተግባራዊ፣ በስነፍቺ እና በስነ ልቦናዊ ንድፈ ሃሳቦች መሰረት ታይተዋል። በተገኘዉ መረጃ
መሰረት በተጠኚዉ አከባቢ አምስት ዛፎች በዋናነት በመጥቀስ በማህበረሰቡ ዉስጥ ያለዉን
መጥፎና ጥሩ እሳቤ እንዲሁም ፋይዳ ጥናቱ ያመላክታል። ማህበረሰቡ ዛፎችን በመለየት ክብር
የሚሰጥበት መንገድ እንዳለዉ እና ዛፎች ማህበራዊ ህይወት እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ
ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸዉ ተረጋግጧል። ዛፎች ተጠብቀዉ እንዲቆዩ እና በተፈጥሯዊ
መንገድ እስካልሞቱ ድረስ ለረጅም አመታት እንዲቆዩ እና እንዳይመነጠሩ ምክንያት የሆነዉ
በተወሰነ ደረጃ ለዛፍ መመንጠር ምክንያት የሆኑ መጥፎ እሳቤዎች ቢኖሩም ግን አብዛኛዉ
ዛፎች እንዳይመነጠሩ የሚረዱ ባህሎች እንዳሉ ጥናቱ ያመላክታል።