Abstract:
በመጀመሪያ ለዚህ ደረጃ እንድበቃ የትምህርት እድሉን ላመቻቸልኝ ለጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው፡፡ በመቀጠልም ለአማካሪዬ ለዶ/ር ሰሎሞን ተሾመ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
ትልመ ጥናት ባቀረብኩበት ወቅት ለጥናቱ የሚሆን ገንቢ አስተያየት በመስጠትና መረጃዎችን
በመጠቆም ለተባበረኝ ረዳት አማካሪዬ ዶ/ር ሞላ ጀምበሬ ልባዊ ምስጋናዬን ይድረስልኝ፡፡
የመስክ መረጃው ተሰብስቦ ለዚህ እንዲበቃ ስለማህበረሰቡ ዳራና ስለ ርዕሰ ጉዳዩ የሚመለከቱ
መረጃዎችን አገኝ ዘንድ ለተባበራችሁኝ እርሻ ገብረማሪያም፣ሺሰማ አዴላ፣ ፀገነት ወልዴ፣ተዘራ
ዘርደዊ፣ሰሎሞን ወልዴ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ በመስክ መረጃ ስብስብ ወቅት በሙሉ ፈቃደኝነት
የጠየቅኳችሁን ሁሉ ከልባችሁ በመመለስ ሥራዬ ምቹ እንዲሆን ሁኔታዎችን ላመቻቻችሁልኝ
መረጃ ሰጭዎቼ ሁሉ ምስጋናዬ ከልብ ነው፡፡ ይህንን ትምህርት እንድማር ብርታት ለሆንሽኝ
መጠሪያሽ ጓደኛዬ በሚል ነገር ግን ከእህትም በላይ ለሆንሽው እህቴና ጓደኛዬ ፍቅርተ ወልዴ
አንቺ ለእኔ ከምገልፅሽ በላይ ነሽና ከልብ አመሰግንሻለሁ ዕድሜና ጤና ይስጥልኝ፡፡
እንዲሁም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተምራችሁ ለዚህ የምርምር ስራ እንድበቃ ላደረጋችሁኝ፤
የተለያዩ መረጃዎች በመስጠትና በመጠቆም ለተባበራችሁኝ ውድ መምህራኖቼ ዶ/ር ሞገስ
ሚካኤል፣ ዶ/ር ዋልተንጉስ መኮነን ከእናንተ የቀለም እውቀት ብቻ ሳይሆን ያገኘሁት መናገር
ከማልችለው በላይ ነውና ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልኝ፡፡ እንዲሁም ዶ/ር አብዩ አስማማው
የተለያዩ መረጃዎች በመጠቆም ላደረክልኝ እገዛ አመሰግናለሁ፡፡
ጥናትና ምርምሩ መስራት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ አይዞሽ በርቺ በማለት
በሞራል ድጋፋችሁ ላልተለየኝ፣ ለወላጅ አባቴ አቶ ከተማ በርታ፣ ውድ እናቴ ወ/ሮ የኔነሽ
ኪዳኔ፣ እንዲሁም በሞራልና በገንዘብ ድጋፋችሁ ላልተለየኝ ወንድሞቼ ጥላሁን ከተማ፤
ሀብታሙ ከተማ፤ሙሉጌታና ሲሳይ ከተማ እንዲሁም ውድ እህቴ ደስታ ከተማ ይህ ጥናት
ለዚህ እንዲደረስና በትምህርቴ ለዚህ እንድበቃ አይዞሽ ባይነታችሁ አልተለየኝምና
አመሰግናለሁ፡፡
ለጥናቱና በእያንዳንዱ የትምህርት እንቅስቃሴዬ ገንዘብ ሲያስፈልገኝ በተለያየ ጊዜ ኪስህን
ያስፈተሸኩህ የእኔ ትክክለኛ “ብርሀን” ወንድሜ ጥላሁን ከተማ አንተ ወንደሜ ብቻ ሳትሆን
‹‹ህይወቴም›› ጭምር ነህ አንተን ማመስገኛ ቃል ያጥረኛል፡፡ እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜ
ከጤና ጋር ይስጥልኝ፡፡ በመጨረሻም በዚህ ክፍል ስማችሁ ያልጠቀስኩኝ ግን በጥናቱና በእኔ
የትምህርት ሂደት ላይ አሻራቹ ላሳረፋችሁ ሁሉ አመስግናለሁ፡፡