Abstract:
ጥናቴን በማረም፣ የተጣመመውን በማቅናት፣ የሳትኩትን በማስታወስ፣ በትጋት እንድሰራበማበረታታት፣ በወቅቱ እንድጨርስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥናቱ ለፍፃሜ እንዲበቃያገዙኝን አማካሪዬን ዶክተር ዐቢዩ አስማማውን እጅግ አመሰግናለሁ፡፡
ረዳት አማካሪዬ ዶክተር አስቴር ሙሉ ደግነት ከፈገግታ ጋር ላልተለየው መስተንግዶዎና ለቀናሃሳብዎ አመሰግናለሁ፡፡
ካላቸው ውድ ጊዜ ላይ ሳይሰስቱ አስተያየት የሰጡኝ ለጥያቄዎቼ ሁሉ ምላሽ ያልነፈጉኝመምህሬ ዶክተር ሞገስ ሚካኤል በጥልቅ ንባብዎ እስክደመምና እስክቀናብዎ ድረስ ሃሳብዎንእየሰጡ መጻሕፈትና የምርምር ሥራዎችን በመስጠትም ድካሜን እያቀለሉ ይህ ሥራእንዲሳካልኝ መንገድ ስለሆኑኝ ምስጋናየ ከልብ ነው፡፡
ይህንን መርሃ ግብር ያለ ክፍያ እንድማር እድል የሰጠኝን የባህር ዳር ዩኒቨርስቲን ስላመቻቸውነፃ የትምህርት እድል አመሰግነዋለሁ፡፡
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በነፃ እንድማር ቢፈቅድልኝም የምኖርበት ቤት እና የምግብወጭየን ያለምንም መሰልቸትና ቅሬታ ሸፍነሽ ያስተማርሽኝ እናቴ ወ/ሮ ተናኜ ንጋቴአመሰግናለሁ፡፡ ብዙ ሰው ልጁን አንድ ጊዜ ሲያስተምር ነው የማየው፡፡ አንቺ ግን እኔን ያለመሰልቸት ደጋግመሽ አስተምረሽኛልና እንዲሁም በዚህ ጥናት ላይ “እኔንም እኮ ይመለከተኛልብለሽ የመረጃ ምንጭ ሆነሽ፣ ጠቋሚም ሆነሽ ላበረከትሽልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡
በመስክ ቆይታዬ መረጃ በመስጠት ጥናቱ እንዲሳካ ቀና ትብብር ያደረጋችሁልኝበአባሪው ክፍል ስማችሁ የተዘረዘረው መረጃ አቀባዮቼ ያለእናንተ ድጋፍ ይህ ጥናት ሊደረግአይችልም ነበር፡፡ ውለታችሁን ሁሌ ስዘክር እኖራለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
ዳንኤል እባቡ ስንት ጊዜ ስልክ እያጠፋሁ ስንት ጊዜ ሰጠኸኝ? አንተ ከጎኔ ባትሆን የዚህንጥናት መረጃዎች በሚገባ የመሰብሰቤን ነገር እጠራጠራለሁ፡፡ ውለታህን እግዚአብሔር
ይክፈልህ፡፡ ከዚህ በላይ ምንም ብልህ ውለታህን ማሳነስ ነው የሚሆነው፡፡
መንገድ መሪዎቼ ሽሽጉ ሙጬና ምስረታው ፍትህአለው በዚያ በጨለማ ብርዱና ዝናቡሳያሰቅቃችሁ አብራችሁኝ ስለወጣችሁና ስለወረዳችሁ ሥራየንም ስላቀለላችሁልኝ እጅግአመሰግናለሁ፡፡
በመጨረሻም ደረጀ ሞላ የኢንተርኔት ወጭ እንዳያሳስበኝ ስላደረከኝ ሳላመሰግንህ አላልፍም፡፡ታናሽ እህቴና ወንድሞቼ ኢየሩሳሌም ወርቁ፣ አማን ሲሳይና ካሳሁን ወርቁ እንደ ታላቅወንድም እኔ ላስተምራችሁ ሲገባ አንተ ተማር ብላችሁ ፍላጎታችሁን ገድባችሁ ያለሰቀቀንእንድማር ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡