Abstract:
“ፋይዲ” ባህላዊ ጋብቻና የሰርግ ሰርዓት በአፋር በራህሌ ወረዳ ማህበረሰብ” በሚል ርዕሰ የቀረበዉ ይህ ጥናት ዋና አላማ አድርጎ የተነሳዉ የ ‘’ፋይዲ” ጋብቻ እና የሰርግ ሰርዓት አከዋወን መመርመር ላይ ነዉ፡፡ የጥናቱን ዋና ዓላማ ከግብ ለማድረሰ የ ”ፋይዲ” ጋብቻ ምንነት መመርመር፣የ “ፋይዲ” የሰርግ ሰነ-ሰርዓት ማሳየት፣ በእያንዳንዱ ሰርዓት ዉሰጥ ያሉ ክዋኔዎች መተንተን፣ ሰርግ ለማህበረሰቡ የሚሰጠዉ ማህበረ-ባህላዊ ፋይዳን መግለጽ የሚሉ ንዑሳን ዓላማዎች አካቷል፡፡ እነዚህን ዓላማዎች መሰረት ያደረጉ መረጃዎች ከቀዳማይ (Primary Source) እና ካልዓይ (Secondary Source) የመረጃ ምንጮች ከተሰበሰቡ በኃላ የማህበረሰቡን ባህል፣አሰተሳሰብና አተገባበር ለማጥናት ሲባልም በኢትኖግራፊያዊ (Ethnographic) የጥናት ስልትን መርሁ አድርጓል፡፡
በጥናቱ መመለሰ ያለባቸዉ ጥያቄዎች ዋናዉን ርዕሰ ጉዳይ መሰረት በማድረግ የጋብቻና የሰርግ ሰነ-ስርዓት ሊያሳይ በሚችል መልኩ ቀርቧል፡፡ መረጃዉን ሙሉ ለማድረግ ሲባል ባህላቸዉንና ቋንቋቸዉን በተመለከተ የተSAለ ግንዛቤ ይኖራቸዋል በሚል ባጋጣሚ፣በእዉቂያና በጥቆማ የተገኙ መረጃ አቀባዮች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በጥናቱ የበራህሌ ማህበረሰብን ይወክላሉ የተባሉ ሶሰት ቀበሌዎች ማለትም ሁለት የገጠር ቀበሌና አንድ የከተማ ቀበሌ (ሻሂ-ጉቢ፣ሌሌ ዓላና በራህሌ 01) ቀበሌዎች በመምረጥ የመሰክ መረጃዎችን በተፎጥሮዓዊ መቼታቸዉ ሶሰት ዓይነት አጋጣሚዎችን በምልከታ፣በቃለ-መጠይቅ እና ተተኳሪ የቡድን ዉይይት መሰረት በማድረግ ከሰላሳ መረጃ አቀባዮች ተሰብሰቧል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎች ለመቀመርና ለማሰማማት ሁለት ንድፈ-ሀሳቦች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ጥምረታዊ ንድፈ-ሀሳብ (Alliance theory) እና ጠቀሜታዊ ንድፈ-ሀሳብ (Functionalism theory) ተግባር ላይ በማዋል በአንዱ ያልተሟላ መረጃ በሌላዉ እንዲሸፈን በማድረግ በጥናቱ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ ከመሰክ መቼቶችም አንጻር ቅንብር ተፎጥሮዓዊ (Natural context) እና አርቲፊሺያል (Artificial context) መቼቶች ተግባር ላይ ዉሏል፡፡ በመረጃ ትንተናዉ በበራህሌ ወረዳ ማህበረሰብ ጋብቻ የተጋቢዎች ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሳይሆን የሁለት ተጋቢዎች ቤተሰብ ወዳጅነትና መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ መሰረት “ፋይዲ” ማለት ፊላጎትን፣ወዳጅትን፣ዝምድና ትስስር መፍጠርን እና የልጅ ቤተሰቦች ለልጃቸዉ ሚሰት የምትሆን ልጅ ከቤተሰቡ ጋር ባላቸዉ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን የቤተሰቡን ዘር በማየት የሚመርጡበት መንገድ መኖሩን አሳይቷል፡፡ በማህበረሰቡ ዉሰጥ ጋብቻ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ፋይዳ መኖሩን መረጃው አሳይቷል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ጥናት በበራህሌ ወረዳ ማህበረሰብ አሰተሳሰብ ጋብቻ ዘር ለመተካት የሚደረግ መሆኑን፣እርሰበርሰ ትሰሰርን፣ማህበራዊ ግንኙነት ማጠናከሪያ እና ዝምድና መመሰረቻ መንገድ እንደሆነም በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም ሰርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ማህበራዊ ኑሮን ማጎልበቻ፣የመደጋገፍና አብሮ የመኖር ዕሴት ማሰቀጠያ በመሆኑ በማህበረሰቡ ዉሰጥ ለትዉልድ ለማሰተላለፍ እና ዕሴቱን ጠብቆ ለማቆየት የሚመለከተዉ አካል ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ጥናቱ ያሳያል፡፡