dc.contributor.author | እንየው በሪሁን | |
dc.date.accessioned | 2020-11-13T06:32:08Z | |
dc.date.available | 2020-11-13T06:32:08Z | |
dc.date.issued | 2020-11-13 | |
dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/11609 | |
dc.description.abstract | አጠቃሎ /አኅፅሮተ ጽሑፍ/ ለዚህ ጥናት የዋለው የገድል መጽሐፍ ገድለ አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላ በሚል ስያሜ የሚጠራ በምዕራብ ጐጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ደብረ ገነት ቍንዝላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሚገኝ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ነው፡፡ ስለኾነም ይህ የገድል መጽሐፍ “ የ ገድለ አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላ ትርጉም እና ጽሑፋዊ ጭብጥ ትንተና ” በ ሚል ርእስ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግእዝ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል የኹለተኛ ዲግሪ ማ ሟያ ጥናታዊ ጽሑፍ ኹኖ ቀርቧል፡፡ የዚህ ጥናት መነሻ ምክንያት ከላይ የጠቀስነው የገድል መጽሐፍ ከጥንታዊ የብራና መጻሕፍት አንዱ እና ብቸኛ ኹኖ ተደብቆ በአብዛኛው የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ አለመታወቁ፤ ከዚህ በፊት በሌሎች አጥኚዎች አለመታየቱ እና አለመጠናቱ፤ በማንኛውም ቋንቋ አለመ ተርጐሙ እና አለመታተሙ፤ ለዚህ ገድል መጽሐፍ አለመታወቅ ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ ስለኾነም ይህ ጥናት እነዚህን ኹኔታዎች መሠረታዊ መነሻ ምክንያት አድርጎ የተደበቀውን የአቡነ ዘካርያስ ዘገሊላን የገድል ሥራ ለሕዝብ እይታ ይፋ ለማ ድረግ እና ለማስተዋዎቅ በትርጉም እና በ ትንተና ጥናታዊ ጽሑፍ መልኩ ተጠንቷ ል፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ ገድለ አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላን በመተርጐም እና በመተንተን ውስጣዊ እና ጥንታ ዊ መልእክቱን ማሳየት እና ማስተዋወቅ ነው፡፡ የጥናቱ ሥነ ዘዴ ገድለ አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላን ለመተርጐም እና ለመተንተን ታሪካዊ ዐይነታዊ የጥናት ዘዴ ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ በዋናነት ይህ የጥናት ጽሑፍ የገድል መጽሐፉ በውስጡ የያዘውን ዋና ጽሑፋዊ ጭብጥ መልእክት እና ዘካርያስ ዘገሊላ እየተባሉ የሚጠሩት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ከልደታቸው ጀምሮ እስከ የሕይዎታቸው ፍጻሜ ድረስ ያለውን ማኅበራዊ፣ መንፈሳዊ የሕይወት ተጋድሎ እና የሠሯቸውን ተኣምራት የሚያሳይ ሲኾን ዘገሊላ የሚለውን ቅጽል ስም ያገኙትም በዐማራ ክልል በሰሜኑ የጣና ሐይቅ ክፍል የምትገኘውን የገሊላ ደሴት ገዳም መሥራች በመኾናቸው ነው፡፡ በጥናቱ የተገኘው ምላሽ ገድሉ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ ሲተረጐም በአብዛኛው የሚያስረዳው በጻድቁ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ነው፡፡ እንደ ሌሎች ገድላት ፖለቲካዊ፣ ዓለማዊ እና ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ብዙ ትኩረት አለማድ ረጉን ነው፡፡ ይህ የገድል መጽሐፍ ቢተረጐም እና ቢታተም ለ አማኝ ኅብረተሰቡ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በምርምሩ መስክም አጥኚዎች በሌላ መል ኩ ጥናት ለማካሄድ ይረዳቸው ዘንድ የሚያገለግል ጽሑፍ ነው | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Geʽez | en_US |
dc.title | የገድለ አቡነ ዘካርያስ ዘገሊላ ትርጉም እና ጽሑፋዊ ጭብጥ ትንተና | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |