Abstract:
አጠቃሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚሰጡት የትምህርት ዐይነቶች መካከል የግእዝ ቅኔ አንዱ እና ዋነኛዉ ነው፡፡ በግእዝ ቅኔ ውስጥም የሥርዐተ ቋንቋ እና የአተረጓጕም ስልት ተካ ት ቶ ይሰጥበታል፡፡ በመኾኑም የግእዝ ቅኔ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እና ለልዩ ልዩ ሐሳብ መግለጫ የሚኾኑ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ይዘቶች ቢኖሩትም በኹሉም ኅብረተሰብ ዘንድ ባለመታወቃቸው አገልግሎቱን ለማሳወቅ የቅኔያትን ይዘት ማጥናቱ አስፈላጊ ነው፡፡ የጥናቱም ዋና ዓላማ በዐፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በተደረጉ እና ለናሙና በተወሰዱ የግእ ዝ ቅኔያት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ይዘታቸውን ማሳየት ሲኾን በገሀዱ ዓለምም ቅኔያት ለዓለማዊ ሥራዎች ማለትም ለልብ ወለድ፣ለፍልስፍና እና ለድርሰት መነሻነት እና ለታሪካዊ እድገት ቀዳሚዉን ቦታ የያዙ እና ወሳኝነት ያላቸው መኾናቸውን ማሳየት ነው፡፡ ጥናቱ የዳሰሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬነዲ ቤተ መጻሕፍት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ ባሉት አብያተ መጻሕፍት በሚገኙት የቅኔያትን ስብስብ የያዙት ን መጻሕፍት በመፈተሽ እና በምዕራብ እና በምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ውስጥ ያሉ ከሦስቱ ዐበይት ቤተ ጉባኤያት ከተመረቁ ሊቃውንት በቃለ መጠይቅ በመጠየቅ ነው፡፡ የጥናቱ መረጃ በዋናነት መጻሕፍትን በመቃኘት እና ቃለ መጠይቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የተሰበሰበው መረጃም በዐይነታዊ የምርምር ዐይነት ሥር ባለው ለገ ላጭ ዐይነታዊ ምርምር የመተርጐሚያ ስልት በኾነው ተርጓሚ የመተንተኛ ዘዴን በመጠቀም ተተንትኗል፡፡ በትንታኔዉም መሠረት የጥናቱ ግኝትም ( ውጤት ) ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ከመኾኑም በተጨማሪ ለድርሰት እና ለፍልስፍና መነሻነት እና ለታሪክ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅ ኦ ያላቸው መኾኑን የቅኔያቱን ይዘት በመተንተን አሳይቷል፡፡ በማኅበራዊ ውስጥም ፡ - ልደት፣ ተስፋ፣ጸሎት፣ ፍላጎት፣ ምክር ፣ ሐሜት፣ ቅንአት፣ ትግዕሥት፣ ስርቆት፣ ማጨት፣ ትዳር፣ ስንፍና፣ ፍርሀት፣ ስደት፣ እንግዳ መቀበል እና ሞት ዐበይት ጉዳዮች መኖራቸውን ሲያ ረጋግጥ በኢኮኖሚ ውስጥ፡ - ማበደር ፣ ማጣት፣ መግዛት፣ መልበስ፣ ንግድ እና ማብላት የሚሉት ዝርዝር ጉዳዮች እንዳሉ አሳይቶ በፖለቲካዊዉ ደግሞ ሹመት፣ ሥልጣን፣ኀይል፣ አስተዳድር፣ ሕግ፣ ፍትሕ እና የፖለቲካዉ መሪ የሚቀመጥባት ቦታ የአዲስ አበባ መገንባትን በግኚቱ አካ ቶ ተንትኗል፡፡ ወደፊትም የግእዝ ቋንቋን በተጨማሪም ማኅበረሰቡ በቅኔያት አገልግሎት ዙሪያ ያላቸውን እሳቤ ለመንፈሳዊ ብቻ ነው እንደሚሉት ሳይኾን ዘርፈ ብዙ ለኾኑት ለልዩ ልዩ ዓለማውያን ሥራዎች መዋላቸውን በትንተናዉ አካቶ ዳሷል፡፡ ቅኔያቱም በምን ዐይነት የአቀራረብ ስልት መቅረባቸውን አይቷል፡፡ በውስጣቸው የታየውን የግስ፣ የፊደል እና የዜማ ልክ ማጥር እና መርዘም አይቶ እንዲስታካከሉ የራሱን አሳብ ሰ ጥቷል፡፡ በአጠቃላይ ጥናቱ ለጥናት አጥኚዎች ስለቅኔያት ታሪካዊ አጀማመር፣ጀማሪ እና ትርጉም እንደመነሻነት አገልግሎት ይሰጣል፡፡