dc.description.abstract |
በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ የሚከወኑ በርካታ መንፈሳዊና ዓለማዊ ከበራዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ከበራዎቹም መካከል አንዱ ሰርግ ነው፡፡ የሰርግ ስርዓተ ከበራዎችም በሚቀርቡበት ማህበራዊና ሀይማኖታዊ አውዶች ምክንያት፣ በተሳታፊዎች ዓይነትና ብዛት እንዲሁም በሚገለጡበት መልክዓምድራዊ ሽፋን የተነሳ ዓይነታቸው እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡
Infact, the word weeding comes from “wed”, the Anglo Saxon word meaning pleadge. Witnesses and public kiss have nearly always been part of the weeding ceremony (Chesser, 2012, p.206).
‘ሰርግ’ ከሚለው ቃል ጋር አቻ ፍች የያዘው ‘Weeding’ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ስርዎ መነሻ “Wed” እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዚህ ቃል ፍቺም፣ “ቃል ኪዳን መግባትን” የሚያረጋግጥና ህዝብ ፊት በመሳሳም መዋደድንና መፈቃቀርን በይፋ ማወጅ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህም በሰርግ ስነስርዓት ውስጥ አንዱ ክፍል እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ በሰርግ ሂደት የመሰሳም ዓላማው ለሰርጉ ቃል ኪዳን መግባትን በማህተም እንደማረጋገጥ ስለሚወሰድ ነው፡፡ ይህ ተግባር አሁን ባለንበት ዘመን ጋብቻውን በህጋዊነት ለማረጋገጥ ፈቃድን መግለጫ ሆኖ ይታሰባል፡፡ ወይም Beeke እንደሚለው ኑሮን በጋራ ለመምራት የሚገባ ቃል ኪዳን መሆኑን ነው (Marriage is simply means that they share the same household (r,2013,P.815).
ከዚህ ጽንሰ ሀሳብ ተነስተን በምዕራባውያን በመሳሳም ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉበትን ሰርግ ወደ ሀገራችን ስናመጣው ለህዘብ ይፋ የሚደረግበት ዓላማው ተመሳሳይ ቢሆንም መንገዱ ግን የተለየ የሚያደርገው ስርዓት አለ፡፡ በሀገራችን ሰርግ ሲደረግ ተቃራኒ ጾታወች ወደ አዲስ ህይወት የሚሸጋገሩበትን እንደየአቅማቸው የምግብና የመጠጥ ዝግጅት በማድረግ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያሳውቁበት ስርዓት ሲሆን መሳሳም የተለመደ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን የተጣማሪወቹ ቤተሰቦች ማህበረሰቡን ጠርተው በአንድ መድረክ በማገናኘት በአንድ ቤት እንዲኖሩና በመተሳሰብ ህይወታቸውን እንዲመሩ የተፈቀደላቸው መሆኑንና በአጋጣሚም ተጣማሪዎቹን በጋብቻ የሚያስባቸው ሌላ ሰው ካለ የተጣመሩና የተያዙ መሆኑን ማሳወቂያ ዝግጅት ነው፡፡
ሰርግ በየትኛውም ማህበረሰብ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የህይወት መሸጋገሪያ ድልድይ ወይም ምዕራፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ወላጆች አሳድገው ለወግ ለማዕረግ አብቅተው ራሱን የቻለ ሌላ ቤተሰብ ይህን ጥናት ለማድረግ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች መነሻ ሆነውኛል፡፡ የመጀመሪያው፣ በሰሜን ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል ጥናት ባለሞያ ሆኘ ለሶስት ዓመት ስሰራ፣ የሀራና አካባቢውን የቀን ቆረጣ እና የትጭጭት ስርዓት ለመዘገብ ታስቦ፣ ከጉባላፍቶ ወረዳ የባህል ባለሞያወች ጋር በመሆን ዶክመንታሪ ፊልሞችን እንዳዘጋጅ ዕድል አጋጥሞኝ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ በርካታ ፎክሎራዊ ክዋኔዎችን እንዳሉና የማህበረሰቡን አኗኗርና ፍልስፍና የሚያሳዩ የተለያዩ አዳዲስ እውቀቶች መኖራቸውን ታዝቤ ነበር፡፡ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ፣ ከሚያዝያ 27 እስከ 30/08 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሄራዊ የባህል ማዕከል አዘጋጅነት፣ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ፣ ዞን አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ሲካሄድ ተገኝቼ በቅንብር ተፈጥሯዊ መቼት የሀራ የሰርግ ስነስርዓት ሲቀርብ የነበሩት ቃላዊ ምልልሶች፣ፉከራዎች፣ምርቃቶች ሁሉ ብዙ የፎክሎር ሀብቶች እንደያዘ
4
ተረድቼ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ይኸንን የበለጸገ ዕውቀት፣ የህይዎት ፍልስፍ የትኛውን የፎክሎር ዘውግ ይዤ ባጠናው ይሳካልኛል የሚል ሃሳብ ነበረኝ፡፡ በመጨረሻ በሰርጉ ውስጥ ማድረግ እንዳለብኝ አስቤ ጥናቴን ወደ በሀራ የሰርግ ስነስርዓት ላይ እንዳተኩር አድርየሚመሰርቱበት በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆች አድገው ከወላጆች ጉያ የሚወጡበትና የራሳቸው |
en_US |