BDU IR

በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ማኅበረሰብ ለቤት እንስሳት ደኅንነት የሚደረግ ሥርዓተ ከበራ በሐምሌ ኪሮስ ማሳያነት

Show simple item record

dc.contributor.author በማተቤ, ጥላሁን
dc.date.accessioned 2024-05-29T13:06:14Z
dc.date.available 2024-05-29T13:06:14Z
dc.date.issued 2015-06
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15819
dc.description.abstract ይህ ጥናት “በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ማኅበረሰብ ለቤት እንስሳት ደኅንነት የሚደረግ ሥርዓተ ከበራ በሐምሌ ኪሮስ ማሳያነት” በሚል ርእስ የሐምሌ ኪሮስ ሥርዓተ ከበራ ክዋኔን በመመርመር ማህበረሰቡ ስርዓተ ከበራውን ለቤት እንስሳት ደኅንነት ማስጠበቂያነት የሚገለገሉበትን እውቀትና ሥርዓት ማሳየት የሚል ዐቢይ ዓላማ ያለው ሲሆን የኪሮስ ስርዓተ ከበራ ሐምሌ ስምንት ቀን የሚከበርበትን ምክንያት መግለጽ፤ ለቤት እንስሳት ደህንነት የሚደረገውን የሐምሌ ኪሮስ ሥርዓተ ከበራ ክዋኔ ሂደት ማሳየት፤ በስርዓተ ከበራ ላይ ያሉ ተምሳሌቶችን መተርጎም፤ ተተኳሪው ማህበረሰቡ ስለ ቤት እንሳሳት ደህንነት ያለውን አመለካከትና እውቀት ማብራራት የሚሉ ንዑስ ዓላማዎች የያዘ ነው፡፡ መረጃዎች በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ የቡድን ውይይት ዘዴዎች በመጠቀም እና 20 ወንዶችን፣ 5 እንስሳት የሚያግዱ (የሚጠብቁ ልጆች /እረኞች) እና 10 ሴቶች በአጠቃላይ 35 የመረጃ ሰጪዎች ተሳታፊ በማድረግ ተሰብስበዋል፡፡ መረጃ ሰጪዎች በዓላማ ተኮር እና በጠቋሚ ናሙና ዘዴ በመጠቀም ተመርጠዋል፤ የተሰበሰቡት መረጃዎች በክዋኔያዊ፣ ማህበራዊ ግንባታ፣ በእንስሳት ደኅንነት ማሕቀፍ እና ስነ ፍች ንድፈ ሃሳቦች ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ በትንታኔው መሰረት የሐምሌ ኪሮስ ስርዓተ ከበራ ለቤት እንስሳት ደኅንነት ተብሎ ሐምሌ ስምንት አባ ኪሮስ ያረፈበትን በማሰብና እግዚአብሔር የገባለትን ቃል ኪዳን መነሻ በማድረግ ማህበረሰቡ የራሱን ሀገር በቀል እውቀትና እሴት በመጨመር የሚከውነው፤ ሃይማኖታዊ በዓል ነው፤ ለስርዓተ ከበራው ክዋኔ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በማዘጋጀት ሐምሌ ስምንት ቀን የተመረጠና ሁሉም አባላት የተስማሙበት ተባእት በግ በማረድ እንስሳት ደም የሚረጩበት የከብቶች ቀን በዓል እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ ስርዓተ ከበራው የራሱ የሆኑ የክዋኔ ሂደቶች እንዳሉት ጥናቱ አሳይቷል፡፡ የሚጠቡ እንቦሶች (ጥጃዎች) በነፃነት ከእናታቸው ጋር የሚውሉበት ቀን እንደሆነ፤ በስርዓተ ከበራው ክዋኔ ዕለት የሚቀርቡ ቁሳዊ ባህሎች በአብዛኛው የእንስሳት ተዋጽኦዎች እንደሆኑ የመስክ መረጃዎች ጠቁመዋል፤ ማህበረሰብ ስለ ቤት እንስሳት ደህንነት የሚከውናቸው በርካታ ልማዶች እንዳሉት ጥናቱ አስረድቷል፡፡ የማህበረሰቡ የቤት እንስሳትን ደህንነት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የሐምሌ ኪሮስ ስርዓተ ከበራ በመፈጸም ስርዓተ ከበራ ለጤና ፈውስ የሚሰጥ መሆኑን ተጠኚው ማህበረሰብ ይጠቁማል፡፡ ይህ መረጃ የጥናቱ ትንተና ክፍል ላይ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም መሰረት ስርዓተ ከበራ የጤና ፈውስ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል፡፡ የሐምሌ ኪሮስ ስርዓተ ከበራ በማህበረሰቡ አባላት ውስጥ አንዳንድ ሰዎች በአባ ኪሮስ ወርሃዊና ዓመታዊ ስርዓተ ከበራ ጊዜ በቤት እንስሳት ላይ የተለያዩ በሽታዎችና አደጋዎች መከሰታቸው እና በአባ ኪሮስ ስም ፀበልና ረፍታቸውን መሰረት በማድረግ በሚፈጽሙት ስርዓተ ከበራ አማካኝነት እንስሳት እንደሚፈወሱ እና በአንዳንድ ሰዎች የደረሰው ችግርና በረከት እንዲደርሳቸውና እንስሳቶች ታመው እንደዳኑላቸው ተጠኚዎች ያብራራሉ፡፡ በመኖር ሂደት ሌሎች ችግሮች እንዳይገጥሟቸው አስቀድመው ለመከላከል እና የተከሰቱ ችግሮችንም ለማስወገድ ሲባል የሚከውኑት ስርዓተ ከበራ እንደሆነ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ ቁልፍ ቃላት፡- ሐምሌ ኪሮስ ከበራ፣ የቤት እንስሳት፣ ደህንነት፤ ሃይማኖትና እምነት en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ማኅበረሰብ ለቤት እንስሳት ደኅንነት የሚደረግ ሥርዓተ ከበራ በሐምሌ ኪሮስ ማሳያነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record