dc.contributor.author | አየሁ, ንጉሴ | |
dc.date.accessioned | 2024-05-08T12:18:33Z | |
dc.date.available | 2024-05-08T12:18:33Z | |
dc.date.issued | 2016-07 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15776 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የአጎላጎሌ ጨዋታ ክዋኔና ፋይዳ በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ማህበረሰብ በሚል ርዕስ ትኩረት ተደርጓል፡፡ የጥናት ዋና ዓላማ የአጎላጎሌ የልጆች ጨዋታ ክዋኔና ፋይዳ ይዘት ተንትኖ ማሳየት ሲሆን የአጎላጎሌ ጨዋታ ሂደቱን መተንተን፣ አጎላጎሌ የልጆች ጨዋታ ክዋኔ ላይ የሚስተዋሉ ቁሳዊ ባህሎች (ትርጉም የሚፈልጉ ጉዳዮች) መመርመር፤ የአጎላጎሌ የልጆች ህግና የሚሰጠውን ፋይዳ መመርመር እና በአጎላጎሌ ጨዋታ ጊዜ የልጆች ቡድን ምስረታና ሚና መጠቆምና ከክዋኔው ጋር በተያያዘ የሚደረሱ ቃል ግጥሞችን መመርመር፤ የሚያሳዩ የምርምር ጥያቄ በማዘጋጅት ቃለ መጠይቅ፣ምልከታ፣ተተኳሪ ቡድን ውይይት በመጠቀም መረጃዎች ተሰብስቧል፡፡ መረጃ ሰጪዎች በዓላማ ተኮር እና በጠቋሚ ናሙና ዘዴ በመጠቀም ተመርጧል፤ መረጃዎች በመቅረጽ ድምጽ፣ በፎቶ ካሜራና በማስታወሻ ደብተር ተሰብሰቧል፡፡ በዚህም መሠረት የአጎላጎሌ ባህላዊ የልጆች ጨዋታ ክብረ በዓሉን ለማክበር ከሚደረጉ ቅድመ ዝግጅት እስከ ክዋኔው መጨረሻ ድረስ ያለውን ክዋኔ ሲከውኑ የሚፈጽሙ ድርጊቶችና ቃል ግጥሞችን ይዘት ለመመርመር በተግባራዊ ንድፍ ሃሳብ፣ በክዋኔ ተኮር ንድፍ ሃሳብና በሰነ ፍች ንድፍ ሃሳብ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት ማህበረሰቡ በክዋኔ አማካይነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሃሳባቸውን በመግለጽ ሲያስተምሩበት፣ ሲመክሩበት፣ ሲዝናኑበት፣ ሃይማኖታቸውንና እምነታቸውን ሲያጸኑበት፣ የማህበረሰቡን ማንነት ሲጠብቁበት መቆየታቸውን በትንተናው ማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ባህላዊ ጨዋታ አማካኝነት ልጆች የወደፊት የሕይወታቸው መሰረት የሆነ ስርዓት የሚለምዱበት፣ ኃላፊነት መቀበልና ተግባራዊ ማድረግን የሚማሩበት፤ የወንድነት ሚና የሚወጡበት እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ በቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰቡ የሚጣልባቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በአካልም ሆነ በእዕምሮ ዝግጁ የሚሆኑበት ሃይማኖታዊ ሆነ ባህላዊ ጨዋታ መሆኑ፣ ጨዋታ የራሱ የሆነ ህጎች ያሉትና ልጆች ከወዲሁ ህግና ደንብ ማክበርን የሚለማመዱበት፣ በጨዋታው ወቅትም የተለያዩ ድርጊታዊ ቧልት ያላቸው ተግባራት የሚከወኑበት፣ ልጆች የሚሰባሰቡበት የራሳቸው መስፈርት እንዳላቸው፣ በሚጫወቱበት ጊዜ የጨዋታውን ህግና ደንብ ተከትለው እንደሚከውኑ፤ በክዋኔው በሚደረሱ የቃል ግጥሞች ይዘት ማሞካሸት፣ማሳሰብን፣ መልካም እድል የሚገልጹ ቃል ግጥሞችን ያለው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ በጨዋታው አማካኝነት እርስ በእርስ መደጋገፍን፣ መረዳዳት፣ ፍቅርን፣ አብሮ መብላትን፣ መጠጣት የሚያዳብሩበት የትውልድ ቅብብሎሽ፣የባህል ስርጭት (መወራራስ) ያለው እንደሆነ በትንተናው ማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨዋታ ላይ ልጆች በአካልም ሆነ በሞራልና በሰነ ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑና ለቀጣዩ ማህበራዊ ኑሮአቸው ልምድ የሚያዳብሩበት ጨዋታ ነው፡፡ የዚህ ጨዋታ ጥናት በተካሄደበት ወረዳ ከሚገኙ 14 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በተወሰኑት አካባቢዎች ክዋኔው እየቀነሰ እንደመጣ በወረዳው ባህልና ቱሪዝም የባህል እሴት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሚኪያስ መለሰ 03/08/2015 ዓ/ም ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም የአጎላጎሌ ጨዋታ ክዋኔ ቀጣይነት እንዲኖረው የወረዳው የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለጨዋታው አስፈላጊውን ድጋፍ፣ ጥናትና ምርምር በማድረግ ቀጣይነት እንዲኖረው ቢያደርግ፤ ጨዋታው እንዲታወቅና ጎብኝዎች እንዲኖሩት ለማድረግም ከመገናኛ ብዙኀንና ከሚመለከታቸው ሌሎች የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር በጋራ ቢሰሩ፤ የመስኩ ምሁራን የበለጠ ሰፊ ጊዜና በጀት በመመደብ የጨዋታው ክዋኔ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ በማጥናት የሚሰጠውን መጠነ ሰፊ ፋይዳ ለማህበረሰቡ ግንዘቤ ቢሰጥ የሚል የይሁንታ ሀሳብ አለኝ፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.subject | Folklore/Cultural Studies | en_US |
dc.title | አጎላጎሌ ጨዋታ ክዋኔና ፋይዳ በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ማህበረሰብ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |