BDU IR

የሃገረሰባዊ እምነቶች ክዋኔና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ የሰርግ ስርዓት ማሳያነት

Show simple item record

dc.contributor.author ደጀን, ታምሩ ገብረመድህን
dc.date.accessioned 2023-07-21T11:38:57Z
dc.date.available 2023-07-21T11:38:57Z
dc.date.issued 2015
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15518
dc.description.abstract ይህ ጥናት ከፎክሎር ዘሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን የሃገረሰባዊ ልማድን በማንሳት የሃገረሰባዊ እምነት ክዋኔና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ የሰርግ ስርዓት ማሳያነት በሚል ርዕስ የቀረበ ጥናት ነው፡፡ በዋናነትም ይህ ጥናት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ ወረዳ የሚኖሩ ማህበርሰቦች በሃዘንም በደስታም ወቅት የተለያዩ ሃገረሰባዊ እምነቶችን ብሎም ትውፉቶችን የተላበሱ ክዋኔዎችን ይከናውናሉ ፡፡ ከእነዚህም መካከል ደግሞ በግንባር ቀደምትነት የሚከወነው የሰርግ ስርዓተ ከበራ ነው፡፡ ስለሆነም የሃረሰባዊ እምነቶች ክዋኔና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ በሰርግ ስርዓት የሚከወኑ ሃገረሰባዊ እምነቶችን ክዋኔና ፋይዳን መተንተን ዋና ዓላማው ነው፡፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ቃለ መጠይቅን፣ምልከታን እና ተተኳሪ የቡድን ውይይትን በመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎነት በመጠቀም በቅድመ ሰርግ ፣በሰርግ ወቅትና በድኅረ ሰርግ የሚከወኑ ሃገረሰባዊ እምነቶችን መረጃ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በጥናቱም የዝቋላ ወረዳ ማኅበረሰብ በሰርግ ስርዓተ ከበራ ወቅት በሚከወኑ ሃገረሰባዊ እምነቶች ድህነትን፣ትምህርትን ፣ስርዓትን ማጽናትና ተግባትን በመገንባት ባህላዊ ትውፊቱን እንደጠበቀ ሲገለገሉበት እንደቀጠሉ በጥናቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ትንታኔውም ሳይንሳዊ የአጠናን ስልት ፣ እና የአሰራር ፈለግን በሚያሳይ መልኩ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡ ጥናቱም ተግባራዊ ንድፈ ሃሳብ፣ስነፍቻዊ ንድፈ ሃሳብ እና ክዋኔዊ ንድፈ ሃሳቦችን የተጠቀመ ሲሆን ጥናቱም በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ተተንትኖ የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም የዝቋላ ማኅበረሰብ ለሃገረሰባዊ እምነቶችን የሚሰጠው ዋጋ ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል ፡፡ የጥናቱ መሰረታዊ ፋይዳም በሰርግ ስርዓተ ከበራ የሚከወኑ ሃገረሰባዊ እምነቶች ለወጣቱ ትምህርትን፣ ለተጋቢዎችም መልካም ተምኔትን የሚተላለፉ ክዋኔዎች በመሆናቸው እና የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ መስተጋብር በማስተካከል በኩል ያላቸው ሚና ከፍ ያለ መሆኑንም ጥናቱ አረጋግጧል። en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title የሃገረሰባዊ እምነቶች ክዋኔና ፋይዳ በዝቋላ ወረዳ የሰርግ ስርዓት ማሳያነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record