Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የተማሪዎችን የማንባብ ፍጥነት በስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች
ተተኳሪነት መፈተሸ ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሰሳካት ገላጭ የምርምር ስልት ጥቅም ላይ
ውሏል፡፡ ጥናቱ በዓላማ ተኮር ናሙና ዘዴ በተመረጠው በወረታ ከተማ አስተዳደር በሁሉም
የመንግስት አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤቶች የተካሄደ ነው፡፡
በተጨማሪም የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች በዓላማ ተኮር ንሞና ዘዴን በመጠቀም የዚህ ጥናት
ተተኳሪዎች ሁነው ተመርጠዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በዕኩል ዕድል ሰጭ እጣ ንሞና
ዘዴ የተመረጡ 59 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ዋና የመረጃ
መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና ነበር፡፡ በተጠቀሰው የመረጃ መሰብሰቢያ የተገኙት መረጃዎች
ተጠናቅረው በመጠናዊ ገላጭ የምርምር ዘዴ በሆነው በገላጭ አተናተን ዘዴ በSPSS
የኮምፒውተር ፕሮግራም ተሰልተው፤ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት
እንደሚያመለክተው የተማሪዎች የማንበብ ፍጥነት ችሎታ አማካይ የማንበብ ፍጥነት (90.55)
ቃላትን በደቂቃ በማንበብ ነበር፡፡ ይህ ውጤትም የሚጠቁመው በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ
የሚገኝ እንደሆነና የማንበብ ፍጥነታቸውም ዝግተኛ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ
ይጠቁማል፡፡ ይህ ደግሞ አንድን ምንባብ በፍጥነት አንብበው ለመረዳት ያላቸው ችሎታ
ዝቅተኛ መሆኑን አሳይቷል፡፡ በጥናቱ የተገኘውን ውጤት በመመርኮዝ የተማሪዎችን የንባብ
ፍጥነት ለማሻሻል አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለማዳበር መምህራን ተማሪዎች የንባብ
ልምዳቸውን አንዲያጎለብቱ ቢያበረታቷቸው፣ የተማሪዎች የዕለት ተዕለት የንባብ ፍጥነት
ብቃትና መሻሻል እየለኩ ድጋፍ ቢያደርጉና ለአማርኛ ቋንቋ ትምሀርት የተመደበው ከፍለጊዜ
በቂ ስላልሆነ የሚስተካከልበት ሁኔታ ቢፈጠር የሚሉ ጠቃሚ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡