BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ የተማሪዎች የማንበብ ፍጥነት ምዘና ጥናት፤ በወረታ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት በስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author አንለይ ዳኛው, ዳኛው
dc.date.accessioned 2023-05-21T11:18:50Z
dc.date.available 2023-05-21T11:18:50Z
dc.date.issued 2015-02
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15275
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የተማሪዎችን የማንባብ ፍጥነት በስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት መፈተሸ ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሰሳካት ገላጭ የምርምር ስልት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ጥናቱ በዓላማ ተኮር ናሙና ዘዴ በተመረጠው በወረታ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤቶች የተካሄደ ነው፡፡ በተጨማሪም የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች በዓላማ ተኮር ንሞና ዘዴን በመጠቀም የዚህ ጥናት ተተኳሪዎች ሁነው ተመርጠዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በዕኩል ዕድል ሰጭ እጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 59 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ዋና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና ነበር፡፡ በተጠቀሰው የመረጃ መሰብሰቢያ የተገኙት መረጃዎች ተጠናቅረው በመጠናዊ ገላጭ የምርምር ዘዴ በሆነው በገላጭ አተናተን ዘዴ በSPSS የኮምፒውተር ፕሮግራም ተሰልተው፤ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያመለክተው የተማሪዎች የማንበብ ፍጥነት ችሎታ አማካይ የማንበብ ፍጥነት (90.55) ቃላትን በደቂቃ በማንበብ ነበር፡፡ ይህ ውጤትም የሚጠቁመው በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነና የማንበብ ፍጥነታቸውም ዝግተኛ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይጠቁማል፡፡ ይህ ደግሞ አንድን ምንባብ በፍጥነት አንብበው ለመረዳት ያላቸው ችሎታ ዝቅተኛ መሆኑን አሳይቷል፡፡ በጥናቱ የተገኘውን ውጤት በመመርኮዝ የተማሪዎችን የንባብ ፍጥነት ለማሻሻል አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለማዳበር መምህራን ተማሪዎች የንባብ ልምዳቸውን አንዲያጎለብቱ ቢያበረታቷቸው፣ የተማሪዎች የዕለት ተዕለት የንባብ ፍጥነት ብቃትና መሻሻል እየለኩ ድጋፍ ቢያደርጉና ለአማርኛ ቋንቋ ትምሀርት የተመደበው ከፍለጊዜ በቂ ስላልሆነ የሚስተካከልበት ሁኔታ ቢፈጠር የሚሉ ጠቃሚ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ የተማሪዎች የማንበብ ፍጥነት ምዘና ጥናት፤ በወረታ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት በስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record