dc.contributor.author | በይርዳው, ግፎ | |
dc.date.accessioned | 2022-12-05T07:57:20Z | |
dc.date.available | 2022-12-05T07:57:20Z | |
dc.date.issued | 2014-05 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14689 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት የጎፋ ዞን ዛላ ወረዳና ሳውላ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ቃልቾች፣ የቃልቻ ቀንና የታላቅነት አሰጣጥ ትውን ጥበባት ገጽታና ማህበረ ባህላዊ ፋይዳ ለማሳየት ያለመ ጥናት ነው፡፡ መረጃዎች ከተለያዩ መዛግብት፣ ከቃልቻ ቀን እና ታላቅነት አሰጣጥ(ለቅሶ) ክዋኔ አውድ በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅ እና ተተኳሪ የቡድን ውይይት፣ በምስል፣ በደምጽና በቪድዮ ተሰብስቧል፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ሲሆን፣ ለመረጃው ትንተና ክዋኔያዊ፣ የጭንቀት ሥርዓተ ከበራ እና የማህበራዊ ማንነት ንድፈ ሃሳቦች ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የቃልቻ ቀን ክዋኔ ሀገረሰብ ሙዚቃና ወዝዋዜ ዘካርሳ፣ የታላቅነት አሰጣጥ(ልቅሶ ክዋኔ) ሙዚቃና ወዝዋዜ ዋማዴ፣ ከሀገረሰባዊ ድራማ አንጻር የቃልቻ ቀን ክዋኔ እና የታላቅነት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ድራማዊ ገጽታ እንደሆኑ መረጃው አሳይቷል፡፡ ዘካርሳ መዚቃ የሚከወነው በዋናነት ረቡዕ አስከ ዐርብ ዕለት ማታ ድረስ መሆኑን፣ በዋናነት በታላቁ ቃልቻ ከዋኝነት የሚቀርብ፣ በታዳሚዎች ጭብጨባ እና ምላሽ እንደሚታጀብ ተረጋግጧል፡፡ የዘካርሳ ውዝዋዜ ከወገብ በላይ የሚቀርብ እና የነጋሪት ምት ተከትሎ፣ የፊት ገጽታ መቀያየር እንደሚታይበት ተገልጿል፡፡ የቀልቻ ቀን(ዐርብ ቀን) ድራማዊ ክዋኔ በውስጡ ግልጽ የሆነ መድረክ፣ ከዋኝ እና ታዳሚ፣ ከፍተኛ የመንፈስ እና የሃሳብ ግጭቶች፣ ታሪክ ነገራ፣ ምልልስና ንግር እንደሚስተዋል መረጃው አሳይቷል፡፡ የታላቅነት አሰጣጥ ክዋኔ የአምልኮ ፈጻሚ ቃልቻ ሲሞት ከለቅሶው ክዋኔ ጋር ጎን ለጎን እንደሚካሄድና የሟችን ታላቅ ልጅ በማንገሥ፣ በሰባተኛው ቀን እንደሚፈጸም ተደርሷል፡፡ ዋማዴ ሀገረሰብ ሙዚቃ ከለቅሶው ቀን 7ኛው ቀን ድረስ በነጋሪት ምት ብቻ የሚቀርብ፣ በቃልቾችና የዋማዴ ልምድ ባላቸው ሰዎች እንደሚቀርብ ተመልክቷል፡፡ ዋማዴ፣ የሚቀርበው በሟች ደጃፍ ባሌ በሚባል ክፍት ቦታ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በሙዚቃውም ስለፈጣሪ ሁሉን ቻይነት፣ የስው ውስንነት፣ በህይወት ስላሉት ቃልቾች፣ እንዲሁም ከሞት በኋላ በአለው ህልውና ላይ ስላላቸው እሳቤ እንደሚነሳ ተገልጿል፡፡ የቃልቻ ቀንና የታላቅነት አሰጣጥ ክዋኔዎች እና የቃልቻ ፎክ ቡድን መካከል ያለው ትስስር ከፍተኛ አንደሆነ ተመልክቷል፡፡ የባህል ቱሪዝም ቢሮዎች ቁርጠኛ የባህል ባለሙያዎች በመመደብ፣ የማህበረሰቡን ባህል በወጉ አስጠንተው በመሰነድ፣ ቀርጾም በዶክመንተሪ ፊልም፣ በመገናኛ ብዙኃንና በመጻሀፍት ተዘጋጅተው ለሌሎች ማሳወቅ ቢቻል የሚል ይሁንታ ቀርቧል፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.title | የቃልቻ ቀን እና የታላቅነት አሰጣጥ ክዋኔ ትውን ጥበባት ገጽታና ማህበረ-ስነ ልቦናዊ ፋይዳ በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳና ሳውላ ከተማ ቃልቾች | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |