dc.contributor.author | በሀና, ደባልቄ | |
dc.date.accessioned | 2022-12-02T07:16:49Z | |
dc.date.available | 2022-12-02T07:16:49Z | |
dc.date.issued | 2015-09 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14687 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት የሴቶችን ሚና ማደላደያ የሚያሳዩ ቃል ግጥሞች መመርመር በሚል ርዕስ ጥናት የተደረገ ነው፡፡ ይህንን ዋና ዓላማ መሰረት በማድረግ ጥናቱ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎችን አካቶ ይዟል፡፡ በቃል ግጥሞች የሚገለጡ የሴቶችን ሚናዎች መለየት፣ማደላደያ ቃል ግጥሞችን መግለፅ እና የሴትንት ሚና ማደላደያ ቃል ግጥሞችን ፋይዳ ማሳየት የሚሉት ናቸው፡፡ ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ ጥናቱ ትኩረት ባደረገበት በደብረታቦር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎች በምልከታ፣ ቃለ መጠይቅና ተተኳሪ የቡድን ውይይት የመረጃ መሰብሰቤያ ዘዴዎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በመስክ ላይ የተሰበሰቡት ቃል ግጥሞች በሁለት ዋና ዋና አርዕስቶች ከተፈጥሮ ወይም ከፆታዊ ሚና እና ከስራ ተሳትፎ የሚገለፁ፣ የሴትነትና ፆታዊ ሚናን የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ የማህበረሰብ ክፍፍሎችን፣ድልድሎችን በሚያሳዩ ልማዳዊ ህጎች መሰረት ሴትን ለማደላደል የሚዜሙ ቃል ግጥሞችን በይዘትና በጭብጥ የተከፈሉ ሲሆን የሚዜሙ ቃል ግጥሞች ደግሞ ጥንካሬን ተሳትፎን የሚገልፁ፣ መልካምነትና ወይም ፆታዊ ሚናን በሚሉ ጭብጣዊ መከፋፈያዎች ከእንስታዊነትና ተግባራዊ ፋይዳቸዉ አንፃር ተደራጅተው ቀርበዋል፡፡ በዚህም ጥንካሬንና ብርታትን የሚገልፁ ቃል ግጥሞች በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መዋቅራዊ ስርዓቶች ከወንዶች በተለየ መልኩ ያላቸውን የጥንካሬ ሚና የሚያሳዩ ናቸው፡፡ መልካምነት የሚያወሱ ደግሞ ከሴትነታቸው ወይም ከፆታዊ አንፃር ለልጅ አስተዳደግ፣ ጥሩ ቤተሰብ ለመመስረትና በመልካም ስነ ምግባር ልጆችን ለማነፅ ያላቸው ጉልህ ድርሻ የሚያሰርፁ ሲሆኑ ስለፆታዊ ሚና የተቀኙ ቃል ግጥሞች ደግሞ የሴትነት ሚናቸውን በስራ፣ በማህበራዊ ግንኙነቶች የመረዳዳትና የመተሳሰብን ፅንስ ሃሳብ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ምድብ በተደረገው ትንተና መሰረት፣ ጥናቱ ከደረሰባቸው ግኝቶች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የጥንካሬና የብርታት ቃል ግጥሞች ሴቶችን በብርታታቸው የሚያደላድሉና የሚያሞግሱ እንዲሁም ከጀግንነትና ከኃላፊነት ጋር ተያይዘው የተተነተኑ ናቸው፡፡ በመልካምነት የቀረቡት ግጥሞች ሴት እናት፣ እህት፣ ሚስት፣ አያት፣አይት ወይም ምራት፣ አክስት፣ ጓደኛና አማት በምትሆንበት ጊዜ ለወንዶች አርያ ስለመሆናቸው ለጥሩ ቤተሰብ መመስረት ሚና መኖራቸውን የሚያሳዩ ናቸው፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.subject | Folklore/Cultural Studies | en_US |
dc.title | የሴትነት ሚና ማደላደያ ቃል ግጥሞች ትንተና በደብረታቦር ከተማ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |