BDU IR

የ"ነሺዳ"ክዋኔና ፋይዳ በዒድ አልፈጥር በዓል እና በሰርግ አዉድ በባህር ዳር ለሁለተኛ ዲግሪ ከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥናት

Show simple item record

dc.contributor.author እስማኤል አህመድ
dc.date.accessioned 2022-11-23T07:13:25Z
dc.date.available 2022-11-23T07:13:25Z
dc.date.issued 2022-09
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14523
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ "የነሺዳ ክወኔና ፋይዳን በዒድ አልፈጥር በዓል እና በሰርግ አዉድ ላይ" መመርመር ነው፡፡በዚህ ዋና ዓላማ ላይ ተመርኩዞ ነሺዳ ምን እንደሆነ?ከዋኞች እነማን እንደሆኑ፣የአከዋወን ገጽታው ምን ይመስላል እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ለምን ተግባር እንደሚከወን ወይም የነሺዳ ክዋኔ ምን ፋይዳ እንዳለው በመመርመር ዝርዘር ዓላማዎችን መልሷል፡፡እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ሊረዱ የሚችሉ ከካልዓይና ከቀዳማይ የመረጃ ምንጮች መረጃዎች ተሰብሰበዋል፡፡በቀዳማይ የመረጃ ምንጭነት ከጥናቱ አካባቢ የመስክ መቼቶች ላይ በአካል በመገኘት በምልከታ፣በቃለ መጠይቅ እና ተተኳሪ የቡድን ዉይይትን በመጠቀም አስር ቁልፍ እና አራት ንኡስ መረጃ ሰጭዎችን በድምሩ አስራ አራት መረጃ አቀባዮች በማሳተፍ ከመስክ መረጃ ተሰብስቧል፡፡የጥናቱ ተሳታፊዎች የተመረጡት በዓላማ ተኮርና በጠቋሚ ናሙና ስልቶች ነው፡፡መረጃዎችን ለመሰብሰብ ደግሞ ቀድመው በተዘጋጁ እና ባልተዘጋጁ ቃለ መጠይቆች አገልግሎት ላይ ዉሏል፡፡ጥናቱ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ሲሆን በገለጻና በይዘት ትንተና ዘዴዎች እንዲሁም በክዋኔያዊና በተግባራዊ ንድፈ ሀሳቦች መተንተን ተችሏል፡፡የነሺዳ አከዋወን ምን እንደሚመስል፣በምን አጋጣሚዎች እንደሚከወን፣ከዋኞቹ እነማን እንደሆኑና ለምን ተግባር እንደሚከወን በእነዚህ ሁለት ንድፈ ሀሳቦች ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ከትንታኔዉም ነሺዳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖቱን አስተምህሮ መሰረት በማድረግ ፈጣሪያቸዉን አላህን እና ነብዩ መሀመድን የሚያመሰግኑበት እና ሀይማኖታዊ አስተምህሮዎችን በነሺዳ ግጥም አማካኝነት መልእክት የሚያስተላለፉበት እንዲሁም ሀይማኖታዊ በዓላትን እና የሰርግ ስርዓቶችን የሚያደምቁበት መሆኑን ጥናቱ ከማሳየቱ ባለፈ ነሺዳ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶችን በማስጠበቅ እና ለትዉልድ በማስተላለፍ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ እንዲሁም ነሺዳ ማህበራዊ እሴቶችን እና መስተጋብሮችን በማጠናከር ረገድ በተለይም መረዳዳትን፣አንድነትን እና መልካም ስነምግባርን በአማኞቹ ላይ እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ነሺዳ ብዙ ጊዜ በወጣት ወንዶች እና ሴቶች የሚዘወተር ሲሆን ክዋኔዉም በመቆም ወይም ደግሞ ወደ ጎን በመሰለፍ እና ክብ በመስራት የትንፋሽም ሆነ የክር ሙዚቃ መሳሪያን ሳይጠቀም በድቤ እና በጭብጨባ እየታገዘ አንዱ ሲያቀነቅን ሌላው እየተቀበለ ይከወናል፡፡ነሺዳ የተለያዩ ተግባራት ያሉት ሲሆን በተለይ በሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በአማኞቹ ላይ ጠንካራ እና የሚስተካከሉ ችግሮችን ለማንጸባረቅ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡ነሺዳ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ስነ ምግባሮች የሚነቀፉበት ጠቃሚ እሴቶቹ ደግሞ በአማኞቹ ዘንድ ሰርጸው ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲሸጋገሩ የሚደረግበት በአጠቃላይ ሀይማኖታዊ አስተምህሮዎችን እንዲተገብሩ፣ማህበራዊ ትስስሮች እንዲጠናከሩ ማህበረሰቡን የመተቸት እና የማስተማር ፋይዳ ያለው ከእስላማዊ ቃል ግጥሞች መካከል ነሺዳ አንዱ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡የነሺዳ መከወን ለእስልምና እምነት ተከታዮች የተጠቀሱት እና ሌሎች ጠቀሜታዎች ስለ ሚሰጥ ሳይበረዝና ሳይበላሽ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ በራሱ ዜማ እና ቅላፄ እንዲከወን የሚመለከተው አካል ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ቁልፍ ቃላት፡-ነሺዳ፣ኒካህ፣አስተምህሮ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title የ"ነሺዳ"ክዋኔና ፋይዳ በዒድ አልፈጥር በዓል እና በሰርግ አዉድ በባህር ዳር ለሁለተኛ ዲግሪ ከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥናት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record