BDU IR

የሴትነት ሚና ማደላደያ ቃል ግጥሞች ትንተና በደብረታቦር ከተማ

Show simple item record

dc.contributor.author ደባልቄ, ሀና
dc.date.accessioned 2022-11-07T11:57:41Z
dc.date.available 2022-11-07T11:57:41Z
dc.date.issued 2015-09
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14309
dc.description.abstract ይህ ጥናት የሴቶችን ሚና ማደላደያ የሚያሳዩ ቃል ግጥሞች መመርመር በሚል ርዕስ ጥናት የተደረገ ነው፡፡ ይህንን ዋና ዓላማ መሰረት በማድረግ ጥናቱ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎችን አካቶ ይዟል፡፡ በቃል ግጥሞች የሚገለጡ የሴቶችን ሚናዎች መለየት፣ማደላደያ ቃል ግጥሞችን መግለፅ እና የሴትንት ሚና ማደላደያ ቃል ግጥሞችን ፋይዳ ማሳየት የሚሉት ናቸው፡፡ ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ ጥናቱ ትኩረት ባደረገበት በደብረታቦር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎች በምልከታ፣ ቃለ መጠይቅና ተተኳሪ የቡድን ውይይት የመረጃ መሰብሰቤያ ዘዴዎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በመስክ ላይ የተሰበሰቡት ቃል ግጥሞች በሁለት ዋና ዋና አርዕስቶች ከተፈጥሮ ወይም ከፆታዊ ሚና እና ከስራ ተሳትፎ የሚገለፁ፣ የሴትነትና ፆታዊ ሚናን የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ የማህበረሰብ ክፍፍሎችን፣ድልድሎችን በሚያሳዩ ልማዳዊ ህጎች መሰረት ሴትን ለማደላደል የሚዜሙ ቃል ግጥሞችን በይዘትና በጭብጥ የተከፈሉ ሲሆን የሚዜሙ ቃል ግጥሞች ደግሞ ጥንካሬን ተሳትፎን የሚገልፁ፣ መልካምነትና ወይም ፆታዊ ሚናን በሚሉ ጭብጣዊ መከፋፈያዎች ከእንስታዊነትና ተግባራዊ ፋይዳቸዉ አንፃር ተደራጅተው ቀርበዋል፡፡ በዚህም ጥንካሬንና ብርታትን የሚገልፁ ቃል ግጥሞች በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መዋቅራዊ ስርዓቶች ከወንዶች በተለየ መልኩ ያላቸውን የጥንካሬ ሚና የሚያሳዩ ናቸው፡፡ መልካምነት የሚያወሱ ደግሞ ከሴትነታቸው ወይም ከፆታዊ አንፃር ለልጅ አስተዳደግ፣ ጥሩ ቤተሰብ ለመመስረትና በመልካም ስነ ምግባር ልጆችን ለማነፅ ያላቸው ጉልህ ድርሻ የሚያሰርፁ ሲሆኑ ስለፆታዊ ሚና የተቀኙ ቃል ግጥሞች ደግሞ የሴትነት ሚናቸውን በስራ፣ በማህበራዊ ግንኙነቶች የመረዳዳትና የመተሳሰብን ፅንስ ሃሳብ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ምድብ በተደረገው ትንተና መሰረት፣ ጥናቱ ከደረሰባቸው ግኝቶች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የጥንካሬና የብርታት ቃል ግጥሞች ሴቶችን በብርታታቸው የሚያደላድሉና የሚያሞግሱ እንዲሁም ከጀግንነትና ከኃላፊነት ጋር ተያይዘው የተተነተኑ ናቸው፡፡ በመልካምነት የቀረቡት ግጥሞች ሴት እናት፣ እህት፣ ሚስት፣ አያት፣አይት ወይም ምራት፣ አክስት፣ ጓደኛና አማት በምትሆንበት ጊዜ ለወንዶች አርያ ስለመሆናቸው ለጥሩ ቤተሰብ መመስረት ሚና መኖራቸውን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ viii ከፆታዊ ሚና አንፃር የቀረቡት ደግሞ ከሴቶች የሙያ ባልትና፣ ማህበራዊ ግንኙነቶች፣ ከቁጠባና ከፆታዊ ሚና ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በአጠቃላይ ቃል ግጥሞቹ የሴቶችን በማህበረሰብ ውስጥ የሚኖራቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ባህላዊና መዋቅራዊ የማደላደያነት ሂደቶችን የሚያሳይ ስለሆነ የሚመለከታቸው የማህበረሰብ አጥኝዎች፣ የታሪክና የስነ ስብ ተመራማሪዎች የስነ ፀሁፍ ባለሙያዎች፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ የፖለቲካና የአስተዳደር ሰዎች ወ.ዘ.ተ ይህንን ጥናት እንደመነሻ በመጠቀም የሴቶችን ፆታዊ ሚና የሚያደላድሉ ቃል ግጥሞችን በሚገባ በማስረፅ ማህበረሰቡን ለማስተዳደርም ሆነ ለእድገትና ለልማት ቢገለገሉበት የተሻለ ይሆናል፤ የሚሉ የመፍትሄ ሃሳቦችም ተቀምጠዋል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title የሴትነት ሚና ማደላደያ ቃል ግጥሞች ትንተና በደብረታቦር ከተማ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record