dc.contributor.author | ንብርት, ብርሃኔ | |
dc.date.accessioned | 2022-08-25T06:37:24Z | |
dc.date.available | 2022-08-25T06:37:24Z | |
dc.date.issued | 2014-06 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14045 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት "የበትር እሳቤ በስማዳ ወረዳ ማኅበረሰብ" ምን እንደሚመስል በመመርመር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ጥናቱ ይዞት የተነሳው ዓላማ በትር በስማዳ ማኅበረሰብ ምን ዓይነት እሳቤ እንዳለው መመርመር ሲሆን፤ ይህንን ጥናት ለማካሄድ ያነሳሱኝ ምክንያቶች፤ ተወልጄ በአደኩበት አካባቢ የሚገኙ ማኅበረሰቦች በትርን ለተለያየ ዓላማና ተግባር ሲጠቀሙበት መመልከቴ ነበር፡፡ ጥናቱ የስማዳ ወረዳ ማኅበረሰብን የበትር እሳቤ መግለፅ፣ የበትርን መጠቀሚያ ዐውድና አገልግሎት መጠቆም፤ የበትርን ትዕምርት/ተምሳሌትነት ማብራራት የሚሉትንንዑሳን ዓላማዎች የያዘ ነው፡፡ ይህንን ጥናት ከግብ ለማድረስ ቀዳማይ እና ካዕላይ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ ከቀዳማይ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ውስጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምልከታና የቡድን ውይይትን በመጠቀም ከመስክ መረጃ ተሰብቧል፡፡ ከመስክ የተገኙትን መረጃዎች በመልክ በልክ በማደራጀት አይነታዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በተግባራዊ፣ መዋቅራዊና ተምሳሌታዊ ንድፈ ሃሳቦች በመታገዝ በገለፃ መልክ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በትንተናው ላይ በትር በማኅበረሰቡ ዘንድ ምን ዓይነት እሳቤ እንዳለው፣ ስለ በትር ዓይነቶች፣ ስለ በትር አዘገጃጀት፣ ስለበትር አውዳዊ አገልግሎት እና ስለ በትር ተምሳሌትነት የሚገልፁ ርዕሶች ተካትተዋል፡፡ በትር በማኅበረሰቡ ውስጥ ከበትሩ አያያዝ፣ አዘገጃጀት፣ ለበትር ከሚሆኑ እፅዋት፣ ከበትሮቹ ዓይነት እና ከበትር አውዳዊ አገልግሎት አንፃር የተለያየ እሳቤ አለው፡፡ ለበትር የሚሆኑ እፅዋት በማኅበረሰቡ ዘንድ የተለዩ እሳቤ አላቸው፡፡ የሙግት፣ የግርማሞገስ፣ የመልካም እድልና የጠባቂነት እሳቤ አላቸው፡፡ የበትር አዘገጃጀትን ስንመለከት ደግሞ ከሚቆረጥበት ወቅት፣ ለማዘጋጀት ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንፃር በትሩ ጠንካራና የሚያምር ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡ የበትር ዓይነቶች በማኅበረሰቦች ዘንድ የእድሜ ክልል ደረጃ ማወቂያ ናቸው፡፡ በትር በተለያዩ አውዶች የተለያየ እሳቤ አለው፡፡ በለቅሶ፣ በሰርግ፣ በሽምግልና፣ በገበያ፣ በዘፈንና ጨዋታ እና በሃይማኖት ቦታዎች ላይ የተለያዩ እሳቤዎች እንዳሉት ጥናቱ ያመለክታል፡፡ በመጨረሻም በትር በማኅበረሰቡ ዘንድ የተለያዩ ተምሳሌቶች ይሰጡታል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.subject | Folklore/Cultural Studies | en_US |
dc.title | Folklore/Cultural Studies | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |