BDU IR

የዘመን ለውጥ በዚገም ማሕበረሰብ፤ በደመራ በዓል አከባበር ማሳያነት

Show simple item record

dc.contributor.author እጅጉ, ታሪክ
dc.date.accessioned 2022-07-01T05:53:20Z
dc.date.available 2022-07-01T05:53:20Z
dc.date.issued 2011-07
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/13858
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ የዘመን ለውጥ እሳቤ በዚገም ማሕበረሰብ፤ በደመራ በዓል አከባበር ሥርዓት ውስጥ ምን እንደሚመስል መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ፣ በዚህ ዋና ዓላማ ላይ ተመርኩዞ አሮጌነት በዘመን ለወጥ እሳቤ ውስጥ ምን እንደሆነ፣ ማሕበረሰቡ ለዘመን ሽግግሩ የሚገለገልባቸውን የመሸጋገሪያ ስልቶችን፣ በዘመን ለውጥ እሳቤ ውስጥ አዲስነት የሚገኝባቸውን ጉዳዮችና በክዋኔዎች ውስጥ የሚስተዋለው የዘመን ለውጥ እሳቤ ለማሕበረሰቡ የሚሰጠውን ፋይዳ በመመርመር ዝርዝር አላማዎች መልሷል፡፡ ጥናቱን ለማካሄድ መረጃዎች የተሰበሰቡት በቀዳማይና ከካልኣይ ምንጮች ነው። ቀዳማይ ምንጮች በምልከታ፣ በቃለመጠይቅ፣ በተተኳሪ የቡድን ውይይትና ቁልፍ የመረጃ አቀባዮችን በጥናቱ በማሳተፍ የተገኙ ሲሆን፣ በመረጃ ምንጭነት ሴት ሰድስት ወንድ አስራሶስት በድምሩ አስራዘጠኝ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎች የተመረጡት በዓላማ ተኮርና በጠቋሚ ናሙና ስልቶች ሆኖ፣ በከፊል ነጻ ቃለ መጠይቅና ውስን ቃለ መጠይቅን በመጠቀም መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በቃለ መጠይቅ የተገኘው መረጃ ትክክለኛ መሆኑን በተፈጥሯዊ መቼት በመስክ ላይ በተካሄደ ምልከታና በተተኳሪ የቡድን ውይይቶች ትክክለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ተተኳሪ ቡድኖች ሦስት ሲሆኑ፣ አንድ ቡድን ስምንት አባላት ያሉት ሌሎቹ ሁለት ቡድኖች ደግሞ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት አባላትን ይዘዋል፡፡ በትንተናው ውስጥ በደመራ ወቅት ሰዎች፣ እንስሳትና እጽዋት ከነበሩበት አሮጌ ህይወት ለመነጠል የተጠቀሙት ቁስ የማሕበረሰቡን የዘመን ለውጥ እሳቤን የሚጠቁም መሆኑ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ አንዳንድ ምግቦች በአዲሱ ዓመት የቡድኑ የግንኙነት ማጥበቂያና ማክበሪያ እንዲሁም፣ የሽግግር ማብሰሪያ ሆነው ታይተዋል፡፡ በአዲሱ ዘመን አዲስነትን የሚወክሉ የምግብ አይነቶችና ልብሶች መጠቀም የቅልቅሉ መሰረታዊ ጉዳይ መሆናቸው ታይቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ ጥናቱ የሚከተሉትን ግኝቶች አምጧል፡፡ እነሱም ከበራውን ምክንያት በማድረግ የቀረቡት ቁሳቁሶች የተሸከሙት የዘመን ለውጥ ሽግግር እሳቤ የማሕበረሰቡ እውቀት፣ አመለካከትና ልማድ ውጤቶች መሆናቸው፤ በደመራ በዓል ሥርዓተ ክዋኔ ሂደቱ ውስጥ የሚከሰቱ ተግባራት የዘመን ለውጥ እሳቤን የሚገልጹ መሆናቸው፤ የዚገም ማሕበረሰብ ለዘመን ለውጡ ምክንያት የሚያደርገው ወቅቶችን ተከትለው የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች መሆኑ፤ ዋና ዋና የጥናቱ ግኝቶች ናቸው፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title የዘመን ለውጥ በዚገም ማሕበረሰብ፤ በደመራ በዓል አከባበር ማሳያነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record