Abstract:
ይህ ጥናት በክልከላና የራስ እስረኛ ልቦለዶች ላይ የተደረገ ስርዓተ ፆታዊ ንባብ ነው፡፡ በሁለቱም
ልቦለዶች ላይ ስርዓተ ፆታ ንድፈ ሃሳብን መሰረት ባደረገ መልኩ ጥናት የተሰራ አለመሆኑ እና
በሁለቱም ልቦለዶች ሴቶችን የላቁ አድርጎ የመሳል ተመሳስሎ ጥናቱን ለማድረግ አነሳሳኝ፡፡ ይህ ጥናት
በሁለቱም ልቦለዶች ላይ ያለው የወንድነትና የሴትነት ተስተማስሎ መፈተሸ አላማው ነው፡፡ በዚህም
መሰረት በሁለቱም ልቦለዶች ላይ የታዩ አቀራረቦች ተመሳሳይነት ታይቶባቸዋል፡፡ ስርዐዓተ ፆታዊ ፅንሰ
ሃሳብ ሴቶችና ወንዶች በስራ ክፍፍል፤ በሃብት ተመጣጣኝነት ሊኖራቸው እነደሚገባ ይገለፃል፡፡
በማንኛውም ስራ ወንዶችም ሆነ ሴቶች በእኩልነት መሰማራት አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ ወንዶችም
ሴቶችም በንብረት የማዘዝና የመምራት ሃላፊነት በእኩል እድል ላይ ሊመሰረት አንደሚገባውም
ይገልፃል፡፡ ሆኖም ግን በሁለቱም ልቦለዶች ላይ አብዛኞቹ ሴት ገፀ ባህሪያት የሀብት ንብረት የበላይ፤
በጋብቻ ውስጥ በእድሜ የላቁ ተደርገው መሳላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡