Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ አይነተ ብዙ (ማሰብ፣ መገመት፣ ማንበብና ማገናኘት) ብልሃት
የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማዳበር ያለውን አስተዋፅኦ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ
የተካሄደው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማንዱራ ወረዳ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት
የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ መረጃው ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ስልትን በመከተል
በመጠናዊ ዘዴ ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ መረጃ በፈተና አማካኝነት ተሰብስቧል፡፡ በዚህ መሰረት
ጥናቱ ለአራት ሳምንታት(10 ስዓት) የተካሄደ ሲሆን፣ ለሙከራ ቡድኑ በብልሃቱ ስልጠና
በመስጠት ትምህርቱን እንዲከታተሉ ሲደረግ፣ የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ በተለመደው
የማስተማሪያ ዘዴ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ የሙከራ ጥናቱ እንደተጠናቀቀ ሁለቱ ቡድኖች ፈተና
እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ አይነተ ብዙ ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማሻሻል
ያለውን አስተዋፅኦ በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት የተሰላ ሲሆን፣ በድህረትምህርት የቁጥጥር ቡድን
አማካይ ውጤት= 11.68 መደበኛ ልይይት= 1.72 እንዲሁም በድህረ ትምህርት የሙከራ
ቡድን አማካይ ውጤት= 15.19፣ መደበኛ ልይይት= 1.56፣ t(60)= 8.435፣ p=.001 d=
2.14 በሁለቱ ቡድኖች መካከል የፍትነቱ ቡድን በለጦ ጉልህ ልዩነት መኖሩን አሳይቷል፡፡
ስለሆነም ብልሃቱ በጥልቀትና በስፋት ቢሰራበት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ
ማዳበርና ጥሩ አንባቢ ማድረግ እንደሚቻል የጥናቱ ውጤት ይጠቁማል፡፡