BDU IR

አይነተ ብዙ (ማሰብ፣ መገመት፣ ማንበብና ማገናኘት) ብልሃት አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማሳደግ አስተዋጽኦ፣ በአስረኛ ክፍል ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author በራሄል አበረ
dc.date.accessioned 2021-09-30T07:19:59Z
dc.date.available 2021-09-30T07:19:59Z
dc.date.issued 2021-09-30
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12676
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ አይነተ ብዙ (ማሰብ፣ መገመት፣ ማንበብና ማገናኘት) ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማዳበር ያለውን አስተዋፅኦ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማንዱራ ወረዳ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ መረጃው ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ስልትን በመከተል በመጠናዊ ዘዴ ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ መረጃ በፈተና አማካኝነት ተሰብስቧል፡፡ በዚህ መሰረት ጥናቱ ለአራት ሳምንታት(10 ስዓት) የተካሄደ ሲሆን፣ ለሙከራ ቡድኑ በብልሃቱ ስልጠና በመስጠት ትምህርቱን እንዲከታተሉ ሲደረግ፣ የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ በተለመደው የማስተማሪያ ዘዴ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ የሙከራ ጥናቱ እንደተጠናቀቀ ሁለቱ ቡድኖች ፈተና እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ አይነተ ብዙ ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማሻሻል ያለውን አስተዋፅኦ በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት የተሰላ ሲሆን፣ በድህረትምህርት የቁጥጥር ቡድን አማካይ ውጤት= 11.68 መደበኛ ልይይት= 1.72 እንዲሁም በድህረ ትምህርት የሙከራ ቡድን አማካይ ውጤት= 15.19፣ መደበኛ ልይይት= 1.56፣ t(60)= 8.435፣ p=.001 d= 2.14 በሁለቱ ቡድኖች መካከል የፍትነቱ ቡድን በለጦ ጉልህ ልዩነት መኖሩን አሳይቷል፡፡ ስለሆነም ብልሃቱ በጥልቀትና በስፋት ቢሰራበት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ማዳበርና ጥሩ አንባቢ ማድረግ እንደሚቻል የጥናቱ ውጤት ይጠቁማል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ- en_US
dc.title አይነተ ብዙ (ማሰብ፣ መገመት፣ ማንበብና ማገናኘት) ብልሃት አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማሳደግ አስተዋጽኦ፣ በአስረኛ ክፍል ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record