BDU IR

ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ሥርዓትና አተገባበር ትንተና በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ

Show simple item record

dc.contributor.author ፈንታ መንግስት
dc.date.accessioned 2021-04-19T07:55:19Z
dc.date.available 2021-04-19T07:55:19Z
dc.date.issued 2021-04-19
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12081
dc.description.abstract ይህ ጥናት የሚያተኩረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ሲሆን “በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ስርዓትና አተገባበር ትንተና” በሚል ርዕስ ተጠንቶ የቀረበ ነው፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ በወረዳው የሚካሄደውን ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ስርዓትና አተገባበር ተንትኖ ማሳየት ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎች በወረዳው የሚከሰቱ ዋና ዋና የእንስሳት በሽታዎችና መንስኤዎችን መለየት፤ በባህላዊ መንገድ የእንስሳት በሽታ መለያና መመርመሪያ ዘዴዎችን መጠቆም፤ መድኃኒት ቅመማ እና አሰጣጥ ስርዓትን ማሳየት የሚሉ ናቸው፡፡እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካት በካልዓይ የመረጃ ምንጭነት ከድህረ ገፅ እና ከተፃፉ ሰነዶች መረጃዎች ተሰብስበው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ከቀዳማይ የመረጃ ምንጮች፤ በምልከታና በቃለ መጠይቅ የተሰበሰበ ሲሆን ይህም በፎቶ ግራፍ፣ በቪዲዮ እና በመቅረፀ-ድምፅ የታገዘ ነው፡፡ ከመስክ የተገኙ መረጃዎች በመልክ በመልክ ተደራጅተው ተቀነባብረውና ተብራርተው በገላጭ የትንተና ዘዴ ተተንትኖ የቀረበ ሲሆን ጥናቱም ዓይነታዊ ነው፡፡ በወረዳው የቀንድ ከብቶችን የሚያጠቁ ዋና ዋና በሽታዎች ተላላፊ፣የወስጥና የውጪ ጥገኛ እና ተላላፊ ያልሆኑ (ድንገተኛ) እንደሆኑ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ የእነዚ በሽታ መንስኤዎች የእንስሳት አያያዝ (አመጋገብና መጠለያ)፣የመኖ አቅርቦት እጥረት፣የሙቀትና ቀዝቃዛ አየር መቀያየር ዋና ዋናዎች ናቸው፡፡ እነዚህን በሽታዎች አክሞ ለማዳን የባህል ህክምና አዋቂዎች በሽታዎችን የሚለዩበትና የሚመረምሩበት ባህላዊ እውቀት የዳሰሰና ለመድኃኒነት በአብዛኛው እፅዋትን ሲጠቀሙ፤ በከፊል ደግሞ የእንስሳት ውጤቶችን ይጠቀማሉ፡፡ የመድኃኒቱ አዘገጃጀት (ቅመማ) በመጨቅጨቅ፣ በመውቀጥ፣ በመደቆስ፣ ወዘተ የሚዘጋጅ ሲሆን አሰጣጡና አጠቃቀም ደግሞ በመጋት፣ በማጠን፣ በመቅባት፣ በማጠብ ከምግብ ጋር በመስጠት እንደሚከወን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በዚህ ወረዳ የባህላዊ እንስሳት ህክምና ተመራጭ የሆነበት ምክንያት፤በውለታ፣በዝቅተኛ ክፍያ፣በምስጋና መተግበሩ፤ በዘመናዊ ህክምና የማይፈወሱ በሽታዎችን ማዳን፤ የባህል ሀኪሞች በቅርበት መገኘታቸው የህክምና ዘርፉን ተመራጭ እንዳደረገው ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በወረዳው ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ዕውቀት ተስተላለፎ በኢ-መደበኛ መንገድ ከቤተሰብና ከጎረቤት በማየት በልምድ የተገኘ መሆኑንና ለሚቀጥለው ትውልድ በሚታሰበውና በሚፈለገው ደረጃ ሊተላለፍ አለመቻሉ ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ትኩረት እያጣ ለመሄድ ምክንያት መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ለዚህ ችግር በመፍትሄነት የተቀመጠ የብልሀተኛ አርሶ አደሮች የሙያ ብልፀጋ በሚል ፕሮግራም በተቀናጀና በተደራጀ ሁኔታ ለማስቀጠል የግብርና፣የጤና ፣ የትምህርት፣ የተፈጥሮ ሀብትና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ቢሰራበት፤ እና ለመድኃኒት በግብዓትነት የሚውሉ የዕፅ ዋት ልማት ቢስፋፋ ለዘርፉም ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ህክምና ጋር ቢቀናጂ የሚል የይሁንታ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject Folklore/Cultural Studies en_US
dc.title ባህላዊ የእንስሳት ህክምና ሥርዓትና አተገባበር ትንተና በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record