BDU IR

ለዛር ሃይል የሚቀርብ የደም መስዋዕት ክዋኔ በላይ ጋይንት ወረዳ

Show simple item record

dc.contributor.author በአድማሱ አገኝ አማረ
dc.date.accessioned 2021-03-23T06:05:41Z
dc.date.available 2021-03-23T06:05:41Z
dc.date.issued 2021-03-23
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12058
dc.description.abstract የሰው ልጅ ከሚያስጨንቀው ቁሳዊና ህሊዊ ጉዳዩ በመነሳት ከሐይማኖቱ ጎን በመቆም ሌሎች የመናፍስት አለምን በድርጊት ሆነ በመንፈሱ ያመልካል። ይህ አምልኮዊ ሂደት ደግሞ እምነት ይሆናል። እምነት ለቆሙለት ነገር ሁሉ መስዋዕት የሚያስፈልገው ጉዳይ ሲሆን መስዋዕቱም እንደ ሁኔታ የተመሰረተ ነው። በተተኳሪ ማህበረሰብ መስዋዕት ከሚቀርብላቸውና ከሚታመኑ መንፈሶች መካከል ኩት ናይል፣ ራሄሎ፣ አዳል ሞቴ፣ ጠቋር መንፈስ ተጠቃሽ ናቸው። ለእነዚህም የዶሮ ደም በማቅረብ እና ሌሎች የምግብና መጠጦ ዝግጅቶችን በመጨመር ልማዳዊ ተግባራቸውን ይከውናሉ፤ ዛሮች እንዲገለጡም ያደርጋል። በመሆኑም ይህ ጥናት ለዛር ሃይል የሚቀርብ የደም መስዋዕት ክዋኔ ትንተና በዋና ዓላማ የያዘና ትኩረት ያደረገ ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ምልከታ፣ ቃለ መጠይቅ እና ተተኳሪ የቡድን ውይይት ለመረጃ መሰብሰቤያነት ውለዋል። ኢላማ ተኮር የንሞና ስልትን በመከተል የተገኙትን መረጃዎችን አውዳዊነታቸውን መሰረት በማድረግ የማረጋገጥ፣ የቅነሳ መተንተኛ ስልቶችን መጠቀም ወይም ትንተና ማድረግ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ከዓብይና ከአጋዥ የመረጃ ምንጮች ስለ ቁስ አዘገጃጃትና አተገባበር፣ ለዛር መስዋዕት የሚቀርቡ የዶሮ አይነቶች ወይም ትርጉማቸውንና ስለሚዘጋጁት ሌሎች የእፅዋዕት አይነቶች ሁሉ የተሰበሰቡትን መረጃዎችን ከስነ ልቦና፣ ከተግባራዊና ከክዋኔ ንድፍ ሃሳቦች ጋር በማዛመድ መተንተን ተችሏል፡፡ ለዛር ሃይል በሚቀርብ የደም መስዋዕት ክዋኔ ላይ የጥናቱ ግኝት የሆኑ እና የማህበረሰቡን ገጽታ የሚገልጹ ሌሎች የእፅዕዋት መስዋዕቶች፣ ለዛር የሚቀርቡ የዶሮ አይነቶች (የሚሸከሙት ትርጓሜ)፣ የሶስት ቀን ተከታታይ ክዎናዎች፣ የቁስ አዘገጃጀትና አተገባበር፣ የአመጋብ ስርዓት፣ የጤና ጥረሽና የመንፈስ ተዋህዶ፣ የጠረጋና የእሳት ረገጣ የሚጠቀሱ ናቸው። በተጨማሪም የዘር ክልከላ፣ የፆታና የምግብ ክልከላ ልማዶች በዋናነት የሚገለጹ ናቸው። ከበራው የማህበረሰቡን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ፋይዳ እንደሚያገኑበት የሚያፀባርቅ፤ የቡድኖችን አንድነት፣ የመከባበር፣ የመረዳዳትና ለቀጣይ ትውልድ ትኩረት መስጠትን በክዋኔው የታዩ ሁነቶች ናቸው። በተጨማሪም የማህበረሰቡን ባህላዊ እና ማህበራዊ፣ አምልኮዊና እምነታዊ ገጽታዎችን የሚያሳይ ከበራ ነው፡፡ በመሆኑም የዘርፉ ምሁራን ቀሪ የፎክሎር እሳቤዎችን የዘርና የምግብ ክልከላ ልማዶችን ቢጠኑ፤ ለባህሉ መዳክም ምክንያት እየሆኑ ያሉትን ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ቢሰጡበት የሚል የይሁንታ መልክቶችን አጥኝው አስቀምጧል። en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject ፎክሎር en_US
dc.title ለዛር ሃይል የሚቀርብ የደም መስዋዕት ክዋኔ በላይ ጋይንት ወረዳ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record