BDU IR

ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ

Show simple item record

dc.contributor.author ከፋለ ዘውዱ
dc.date.accessioned 2021-03-18T10:35:02Z
dc.date.available 2021-03-18T10:35:02Z
dc.date.issued 2021-03-18
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12051
dc.description.abstract ይህ ጥናት በሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤን በመተንተንና በማብራራት የማህበረሰቡ አባላት በህይወት ዑደታቸው ውስጥ የምርት መቀነስ እንዳይገጥማቸው የተለያዩ ልማዳዊ እምነቶችን በአዝመራቸው ላይ በመፈፀም ምርታቸው እንዴት እንደሚጨምር እሳቤያቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም ጥናቱ የሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ ምርት ላይ በረከት ማግኘትና ማጣትን የሚያመጡ የመልካም መናፍስትን ሃይል የማስደሰትና የእኩይ መናፍስትን ሀይል ለመከላከል ሲሉ የሚፈፅማቸውን ሀገረ ሰባዊ እምነቶችን የፈተሸ ነው፡፡ በተጨማሪም ለልማዳዊ የምርታማነት መጨመሪያ ስልት ተደርገው የሚታሰቡ ቁሶችና ሀሳቦችን የስነ ፍች ገፅታዎች እንዲሁም ለምርት በረከትን ያሳጣሉ ወይም ይቀንሳሉ ተብለው በማህበረሰቡ ዘንድ የተከለከሉ ልማዳዊ እምነቶችን ምክንያት ማብራሪያና ትንታኔ ተሰጥቷል፡፡ እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የጥናቱ ዝርዝር ዓላማዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ከቀዳማይ እና ካዕላይ የመረጃ ምንጮች በተፈጥሯዊ አውድ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ ቀዳማይ መረጃዎች ከፎክሎር የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች መካከል በምልከታ፣ በቃለ-መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ውይይት የተሰበሰቡ ሲሆን ካዕላይ መረጃዎች ደግሞ በመዛግብት ፍተሻ ተካተዋል፡፡ለዚህም ከመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች መካከል ቪዲዮ ካሜራ፣ ፎቶ ካሜራ፣ መቅረፀ ድምፅ አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ በተጨማሪም ከመስክ የተገኙ ጥሬ መረጃዎችን ለመመዝገብ ማስታወሻ ደብተሮች ስራ ላይ ውለዋል፡፡ የዚህ ጥናት አካላይ ሆኖ የተመረጠው አካባቢ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ካሉት 27 የገጠር ቀበሌዎችና 5 የከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤቶች ውስጥ ሳንክራ ገነታ እና ሊበን ዳንኩራ በሚባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከሁለቱም ቀበሌዎች 25 መረጃ አቀባዮች በዓላማ ተኮር የናሙና ስልት ተመርጠው ለጥናቱ የሚሆኑ መረጃዎችን በመስጠት የተካተቱበት ነው፡፡ መረጃዎችን ከላይ በተገለፀው መልኩ ለመሰብሰብና ለመተንተን የጠቀሜታዊነት እና ስነ-ፍች ንድፈ ሀሳቦች ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ ጥናቱ የሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ ምርቱ ላይ የአበርክት መንፈሱ በረከት ይሰጣል በማለት ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤዎችን የሚተገብሯቸው በሁለት አብይ ምክንያቶች እንደሆነ አመላክቷል፡፡ የመጀመሪያው የአበርክት መናፍስቱን የመማፀንና የመለማመጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአበርክት መናፍስቱን ሀይል ይገዛሉ ወይም ይማርካሉ የተባሉ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመፈፀም መናፍስቱን ማታለልና መለማመን የሚሉት አንኳር ውጤቶች ታይተዋል፡፡ በዚህም ጥናቱ የሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤዎች ምን እንደሚመስል ከማህበረሰቡ አተያይና አረዳድ አኳያ ያለውን እምነትና አተገባበር ያመላከተ ነው፡፡ ይህ ልማዳዊ እምነት በማህበረሰቦች ዘንድም ይሁን በግለሰቦች በአስገዳጅነት ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎት በመነሳት በምርቱ ላይ መረከት እንዲያወርድ ወይም እንዲሰጥ በማለት የሚተገብሯቸው ልማዳዊ እምነቶችንና ለምርቱ መበርከት ምክንያት የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመገልገያና ለአበርክት መንፈሱ ማታለያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቁሳ ቁሶችን እንደሚፈፅሙ የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ በመሆኑም በዚህ ማህበረሰብ ዘንድ ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤ በምርት ላይ በረከት ማጣትና ማግኘት ምክንያቱ የመናፍስት ሀይል ነው በማለት የማይለወጡና የማይቀሩ ልማዳዊ እምነቶች እንዳሉና አሁንም በማህበረሰቡ ተፈፃሚነት እንዳላቸው ለማየት ተችሏል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject ፎክሎር en_US
dc.title ልማዳዊ የምርታማነት መጨመር እሳቤ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ማህበረሰብ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record