dc.contributor.author | ቃልኪዳን ግርማው | |
dc.date.accessioned | 2021-02-18T07:48:51Z | |
dc.date.available | 2021-02-18T07:48:51Z | |
dc.date.issued | 2021-02-18 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/11907 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት የዘጌ ማህበረሰብን የስእለት ልምድ ተከታታይነትና ለውጥ በመተንተን የማህበረሰቡ አባላት በህይወታቸው ውስጥ የከበደ ችግር በገጠማቸው ጊዜ ለፈጣሪያቸው ስእለት በማድረግ ችግራቸውን እንዴት እንደሚያቃልሉ የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም ጥናቱ በዘጌ ማህበረሰብ የስእለት ልምድ ውስጥ ግለሰቦች ለምን ዓላማ ስእለት እንደሚያደርጉ፣ በስእለት ልምድ ውስጥ ስለሚታዩ ተከታታይ ገፅታዎች፣ ስለተከሰቱ ለውጦችና ስለለውጡ ምክንያቶች ተተንትኗል፡፡ እነዚህን መሰረታዊ የጥናቱ ዓላማዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመጀመሪያ የመረጃ ምንጮች በተፈጥሯዊ አውድ ማለትም በምልከታ፣ በቃለ-መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ውይይት የተሰበሰቡ መረጃዎች በመዋቅራዊ ጠቀሜታዊነት እና በስነ-ልቦና ንድፈ ሀሳቦች መነፅርነት ተፈትሸዋል፡፡ የጥናት አካባቢ ሆኖ የተመረጠው የዘጌ ማህበረሰብ ዘጌ 01፣ ኡራ ኪዳነምህረት እና ይጋንዳ መሐል ዘጌ በሚባሉ ሶስት ቀበሌዎች የተዋቀረ ነው፡፡ በመሆኑም ከሶስቱም ቀበሌዎች 33 መረጃ አቀባዮች በዓላማ ተኮር የናሙና ስለት ተመርጠው በጥናቱ ተካተዋል፡፡ ጥናቱ የዘጌ ማህበረሰብ የስእለት ልምድ በሁለት አብይ ምክንያቶች እንደሚደረግ አመላክቷል፡፡ የመጀመሪያው ግለሰቦች በህይወታቸው ውስጥ የሚገጥማቸው ፈተና ሲሆን ችግሩን ለማለፍ ለፈጣሪቸው ስእለት ለማድረግ ያስገድዳቸዋል፡፡ ሁለተኛው ስእለት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እምነት ውስጥ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች እንዲፈፅሙት አስገዳጅ ስርዓት ባይሆንም ቤተ ክርስትያኗ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መንፈሳዊ መቀናናት እንዲፈጠር ስእለቱ በአደባባይ እንዲነገር በማድረግ ታበረታታለች፡፡ በሌላ መልኩ ስእለት ለመፈፀም የሚያስገድዱ ችግሮች ዘመኑ በወለዳቸው ቴክኖሎጂዎች እየተፈቱ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በማህበረሰቡ የስእለት ልምድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኑሮ ዘይቤው ላይ ለውጥ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.subject | Folklore/Cultural Studies | en_US |
dc.title | ተከታታይነትና ለዉጥ በዘጌ ማህበረሰብ የስእለት ልምድ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |