Abstract:
አህጽሮተ ጥናት
የጥናቱ አብይ አላማ መር የመጻፍ ክሂልን የማስተማሪያ ብልሀት የተማሪዎችን የመጻፍ
ችሎታና ተነሳሽነት በማጎልበት ረገዴ ያሇውን ሚና መፈተሽ ነበር፡፡ የጥናቱ አካባቢ በዯሴ
ከተማ፣ ሆጤ ከፍተኛ ሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርትቤት ነው፡፡ ትምህርትቤቱ የተመረጠው በአመቺ
ናሙና ዘዳ ነው፡፡ በዚሁ ትምህርት ቤት በ2010 ዓ.ም በ11ኛ R7 የሚማሩ ተማሪዎች በእኩል
እዴል ሰጭ በሆነው በምዴብ የእጣ ንሞና ዘዳ (Cluster Sampling) ሲሆን ጥናቱ ፍትነታዊ
(የአንዴ ቡዴን ቅዴመና ዴህረ) ነው፡፡ ሇመረጃ መሰብሰቢያ ፈተናና የጽሁፍ መጠይቅ
አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ የቅዴመትምህርት የመጻፍ ፈተና የተሳታፊዎችን ዲራዊ የመጻፍ
ችሎታን ሇመሇካት ተግባራዊ ተዯርጓል፡፡ ሇአራት ሳምንታት በተከታታይ ሇጥናቱ ተሳታፊዎች
ትምህርት ከተሰጠ በኋላ ተሳታፊዎች በተሠጠዉ ትምህርት ያሳዩትን የመጻፍ ችሎታ ሇውጥ
ሇመሇካት በዴህረትምህርት ፈተና መረጃ ተሰብስቧል፡፡ መረጃውም በጥንዴ ናሙና ቲ-ቴስት
ተተንትኗል፡፡ በውጤት ትንተናውም በቅዴመና ዴህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል
ጉልህ ልዩነት (P<0.001) ታይቷል፡፡ ይህም የተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ መሻሻለን
አሳይቷል፡፡ በተመሳሳይ የጥናቱን ተሳታፊዎች የመጻፍ ተነሳሽነት ሇመፈተሽ ቅዴመትምህርት
የጽሁፍ መጠይቅና ትምህርቱ ከተሰጠ በኋላ የመጣውን ሇውጥ ሇማወቅ የዴህረትምህርት
የጽሁፍ መጠይቅ በጥናቱ ተሳታፊዎች ተሞልቷል፡፡ መረጃውም ተዯራጅቶ በጥንዴ ናሙና ቲ-ቴስት ተተንትኗል፡፡ በውጤቱም በቅዴመና ዴህረትምህርት የመጻፍ ተነሳሽነት የጽሁፍ
መጠይቅ አማካይ ውጤት መካከል በስታትስቲክስ ጉልህ (P<0.001) ልዩነት ታይቷል፡፡ ይህም
በመር መጻፍን ማስተማሪያ ብልሀት የመጻፍ ትምህርትን መማር የመጻፍ ተነሳሽነትን
በማሳዯግ ረገዴ አዎንታዊ ሚና ስላሇው በመፍትሄነት ተጠቁሟል፡፡